የኦሮሚያ አደጋ ስጋት ሥራ አራር ኮሚሽን አልሚ ምግብ ለማጓጓዝ የወጣ ግልጽ ጨረታ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር CSB/59/2014
አልሚ ምግብ ለማጓጓዝ የወጣ ግልጽ ጨረታ
የኦሮሚያ አደጋ ስጋት ሥራ አራር ኮሚሽን ለሲ.ኤስ.አይ ፕሮግራም ተጠቃሚዎች አገልግሎት የሚውል አልሚ ምግብ ከአዳማና ድሬዳዋ ከሚገኘው የዓለም ምግብ ፕሮግራም መጋዘን ወደ ቦረና ባሌ ጉጂ ምዕራብ ጉጂ ምዕራብ ባሌ ዞኖች ውስጥ ለሚገኙ የፕሮግራሙ ተጠቃሚዎች ለአንድ ዓመት በየወሩ በግምት 2865.22 ኩንታል ተረጂዎች ወደሚገኙበት ወረዳዎች ለማጓጓዝ ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተገለጹ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል።
በመሆኑም ተጫራቾች፦
- ለዘመኑ የታደሰ የሥራ ንግድ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ የግብር ግዴታ ለመወጣቱ ከሀገር ውስጥ ገቢ ባለሥልጣን ወይም ጉዳዩ ከሚለከታቸው አካላት የተሰጠ የጽሑፍ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ከሚለከተው የመንግሥት መ/ቤት የሥራ ግብርና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ።
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘረውን የአልሚ ምግብ መጠን ለማጓጓዝ ለውድድር ሲቀርብ ከትራንስፖርትና መንገድ ባለሥልጣን /ቢሮ የታደሰ የደረጃ ብቃት ማረጋገጫ ምዝገባ ፈቃድ ፎቶ ኮፒ የማቅረብ ግዴታ አለበት።
- የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከቢሮ ቁጥር 20 ብር 100 በመክፈል መውሰድ ይቻላል።
- የጨረታ ኤንቨሎፖቹን ኦሪጂናል እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በታሸ ኤንቨሎፕ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 13 በመምጣት ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በኤንቨሎፑ ለየብቻ አሽገው የድርጅታቸውን ሙሉ አድራሻ መግለጽ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ4:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በ4:30 ሰዓት ላይ ተራጫቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሚሽኑ አዳራሽ የሚከፈት ሲሆን 16ኛው ቀን በል ወይም የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።
- የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) የጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም CPO ከጨረታ ሰነድ ጋር በፖስታ ታሽጎ አብሮ ይቀርባል።
- ጨረታውን አሸንፈው ውሉን ሲፈርሙ ላሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10% የሥራ አፈጻጸም ዋስትና CPO ወይም በባንክ በተረጋገጠ ቼh ቅድሚያ ያስይዛሉ።
- አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው።
- በአንድ ወረዳ ሥር ላሉት ማራገፊያ ጣቢያዎች ሁሉም ላይ ዋጋ ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውጪ ይሆናል።
- ተጫራቾች በእያንዳንዱ የወረዳ ከተማ እና በወረዳ ለሚገኙ የማሰራጫ ጣቢያዎች በአንድ ዙር ለአንድ ኩንታል የሚጠይቁትን አማካኝ ነጠላ ዋጋ እና አጠቃላይ ዋጋ ለየብቻ መግለጽ አለባቸው።
- በየወሩ የሚጓጓዘው የአልሚ ምግብ ጠን ሊጨምርም ሊቀንስም ይችላል።
- ተሽከርካሪ በማይደርስበት ጣቢያ ተጫራቾች በጋማ ከብት የማድረስ ሀላፊነት አለባቸው።
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-442-61-69 ላይ በመደወል መጠየቅይቻላል።
አድራሻ: ሣሪስ አዲስ ጎማ /ሆራይዘን/ ፋብሪካ ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር 011-442-7770
ቡሳ ጎኖፋ ኦሮሚያ
ፊንኔ
የኦሮሚያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን
