Tender Detail

Tender Details

  • Deadline15 Aug 2022, 9:32 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) ከ2022 እ.ኤ.አ. በጀት ዓመት ጀምሮ ለ3 ዓመታት የድርጅቱን ሂሳብ ኦዲት የሚያደርጉ ተገቢውን መስፈርት የሚያሟሉ የኦዲት ድርጅቶችን አወዳድሮ የአገልግሎት ስምምነት መፈጸምና ማሰራት ይፈልጋል


የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ)

የኦዲት ጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ) በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሰረት አገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት ሆኖ በምዝገባ ቁጥር 1146 ተመዝግቦ የሚንቀሳቀስ መንግስታዊ ያልሆነ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ሲሆን ከ2022 እ.ኤ.አ. በጀት ዓመት ጀምሮ ለ3 ዓመታት የድርጅቱን ሂሳብ ኦዲት የሚያደርጉ ተገቢውን መስፈርት የሚያሟሉ የኦዲት ድርጅቶችን አወዳድሮ የአገልግሎት ስምምነት መፈጸምና ማሰራት ይፈልጋል።

የማመልከቻ መስፈርቶች

  • የንግድ ፈቃድ
  • የታደሰ የሞያ ማረጋገጫ ፈቃድ
  • የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማረጋገጫ
  • የሥራ ልምድ መግለጫ በተመሳሳይ ተቋማት ላይ በቂ የኦዲት ልምድ ያለው
  • የግብር መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት
  • ለየዓመቱ በ(2022 ፣ 2023 እና 2024) ለአገልግሎት የሚጠይቁትን ክፍያ/ለስራው የሚያቀርቡበት ዋጋ
  • የበጀት ዓመቱ የኦዲት ስራውን የሚያጠናቅቁበት ጊዜ እና
  • ሌሎች በኦዲት ተቋማት ላይ የተጣለውን የህግ ግዴታ የምታሟሉ

ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የምታሟሉ የኦዲት ድርጅቶች በሚከተለው አድራሻ የማይመለስ መወዳደሪያ ሰነዶቻችሁን እስከ ሐምሌ 22/2014 ዓ.ም. ድረስ ከታች በተቀመጠው ኢሜይል አድራሻ በማመልከት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ስልክ 251 11 868 5705

ኢሜይል- Info@ehrco.org  or ehrcovacancy2022@gmail.com

Save Tender