የመኪና ሽያጭ ማስታወቂያ
ማስታወቂያ
በአፈጻጸም ከሳሽ አቶ ተክሌ ነዋይ እና በአፈጻጸም ተከሳሾች:- 1ኛ አቶ ዘውዴ ሀይሉ፣ 2ኛ. አቶ መለስ ጥላሁን መካከል ስላለው የገንዘብ አፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ ላይ በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በሀገረ ማርያም ወረዳ በሾላ ገበያ ቀበሌ ውስጥ ንብረትነቱ የአቶ ዘውዴ ሀይሉ የሆነውን ኮድ 03- 15264 አ.ማ መኪና በመነሻ ዋጋ 273,936 (ሁለት መቶ ሰባ ሦስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ ስድስት ብር) ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረታ የወጣ መሆኑን በግለጽ ጨረታ እንድታወጡ እና ጨረታው ጋዜጣው ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት በአየር ላይ እንዲውል በማድረግ አንዲሁም ፍ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው የማይገደድ ሆኑን እና ጨረታውም የሚካሄደው ንብረቱ በሚገኝበት በሀገረ ማርያም ወረዳ በሾላ ገበያ ቀበሌ መኪናው ታግዶ ቆሞ በሚገኝበት የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ነሐሴ 2 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ጀምሮ መሆኑን እና በዕለቱ በቀረበው ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ የሚሸጥ ሆኑን ገልጻችሁ ለፍርድ ቤቱም ጨረታውን በጋዜጣ ላይ ማውጣታችሁ እንድታሳውቁን ሲል የሀገረ ማርያም ወረዳ ፍርድ ቤት አዟል።
አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጠቅላይ ፍርድ ቤት በሰሜን ሸዋ
ዞን ሀገረ ማርያም ወረዳ ፍርድ ቤት
