የመኪና ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት እነ አቶ ዳዊት አብርሃ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ጉዕሽ ካሳ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌ/ጠ/ፍ/በ/መ/ቁ/2112271 በ30/5/2014 ዓ.ም. እና የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/284385 በ30/7/2014 ዓ.ም. በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ቶኩማ የመኪና ማቆሚያ ጊቢ የሚገኝ የሠ/ቁ/ኮድ3-34022 አ/አ የሆነ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 150,000 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) የስም ማዛወሪያ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 5 ቀን 2014 ዓ.ም. በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 4፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን ፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በባንክ በተረጋገጠ C.P.O. ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት። በተጨማሪ ተጫራቾች ካፒታል ጌይን እና ታክስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ ፣ ሐራጁ ጐድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬክቶሬት የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን።
በፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት
