የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የ2015 በጀት አመት የቢሮ ፅዳት አዉት ሶርስ ግዥ / አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት የ2015 በጀት አመት የቢሮ ፅዳት አዉት ሶርስ ግዥ / አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች፦
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው በሙያዉ የተሰማሩ፣
- . የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፣
- የሚሳተፉ ተጫራቾች የእቃ /አገልግሎቱ/ ዋጋ ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሽህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚገዙ እቃዎች /አገልግሎቶች / አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን / ከጽ/ቤቱ ቢሮ 33 ከጨረታ ሰነዱን ማግኘትና ማየት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 200 ( ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 33 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ዋጋ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ የሚፈልጉ ለጽ/ቤቱ ገንዘብ ያዥ በመክፈል ደረሰኙን ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ መሆን አለበት። በርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ግዥ፣ ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክተር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 30 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ጨረታው በጋዜጣ በግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ፣ ፋይ/ንብ/ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 30 በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጐ በዚዉ ቀን 4፡00 ላይ ይከፈታል።
ይሁን እንጂ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጽ/ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብት አለው። - ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 30 በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 058 220 1068 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058 220 2030 ወይም 058 220 0924 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
የአብክመ ርአሰ መስተዳድር ጽ/ቤት
