የሸጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል አገልግሎት የመኪና ጎማ ፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃ፣ የኦአር ጫማ ፣ የጽዳት እቃ ፣ የኦክስጅን ሙሊት ከመኪና ጭነት ጋር እና ተደራራቢ አልጋ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የሸጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል አገልግሎት የሚውል ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ
- የመኪና ጎማ ፤
- የኤሌክትሮኒክስ እቃ፣
- የኦአር ጫማ፣
- የጽዳት እቃ፤
- የኦክስጅን ሙሊት ከመኪና ጭነት ጋር እና ተደራራቢ አልጋ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም፡-
- ተጫራቾች እቃዎችን ወይም አገልግሎቾችን ለማቅረብ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያወጡ የተሰጣቸው ፈቃድ አንድ አመት የሞላው ከሆነ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /ቲን/ ያላቸው መሆኑን የሚያረጋገጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከአሁን በፊት የመንግስት ግዥዎች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸው ተገልፆላቸው ቀርበው ውል ለመያዝ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ወይም ውል ይዘው በአግባቡ ባለመፈፀማቸው እርምጃ ያልተወሰደባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ ወይም ለመወዳደር የሚወጡ ወጭዎች ቢኖሩ መ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰዱን የማይመለስ ብር 40(አርባ ብር) ከገንዘብ ያዥ በመክፈል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውንና ደጋፊ ማስረጃቸውን የሚያዘጋጁበት ቋንቋ በአማረኛ መሆን ይኖርበታል፡፡
- በዚህ ጨረታ መጫረት የምትፈልጉ በማያሻማ ሁኔታ በመሙላት ጨረታው በበኩር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሸጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ በ4፡00 ይከፈታል፡፡
- አንድ ተጫራች በወጣው የጨረታ ሰነድ ላይ ጥያቄ ወይም ማብራሪያ ቢያስፈልግ ጨረታውን ላወጣው መስሪያ ቤት በፅሁፍ ወይም በፋክስ ቁጥር 0586610264 ወይም በስልክ ቁጥር 0586610330 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡ ጨረታውን ያወጣው መስሪያ ቤትም የተጠየቀውን ጥያቄ ማብራሪያ የሚያሰጥ ሆኖ ሲገኝ ለሁሉም ተጫራቾች በጽሁፍ ወይም በፋክስ ጨረታው ከመከፈቱ ከ5 ቀናት በፊት መልስ ይሰጣል፡፡
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- በተጫራቾች መመሪያ ይዘት ላይ ምንም ማሻሻያ ማድረግ አይቻልም፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን እሁድ ቅዳሜና በዝግ ቀን ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን በተጠየቀው ስዓት የሚከፈት መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች አሸናፊ ከተለየ በኋላ የሚመለስ ለእያንዳንዱ ብር 4,000 (አራት ሺህ ብር) ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
የሸጋው ሞጣ ጠቅላላ ሆስፒታል
