ኦሜዳድ ኃላ/የተ/የግ/ ኩባንያ ያገለገሉ መኪኖችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
ያገለገሉ ልዩልዩ መኪኖች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ኦሜዳድ ኃላ/የተ/የግ/ ኩባንያ ያገለገሉ መኪኖችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። በዚህም መግዛት የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ጥቅል መደብ
/ሎት/ መሠረት እንድትሳተፉ ይጋብዛል።
- ሎት አንድ ልዩ ልዩ መኪኖች
የጨረታ መስፈርቶች፦
1. ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሃያ /20/ ቀናት በቅሎ ቤት ቴሌ ጋራዥ ፊት ለፊት ቶታል ነዳጅ ማደያ አጠገብ ካለው ኦሜዳድ ቅርንጫፍ አንድ መቶ ብር (100.00) በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
2. ተጫራቾች የመኪናዎችን አይነትና ዝርዝር በአካል ማየት ከፈለጉ ዱከም ከተማ ቀደም ሲል ገደራ ሆቴል በነበረው ፊት ለፊት በሚያስገባው አስፓልት መንገድ 200 ሜትር ገባ ብሎ ቄራው አጠገብ በሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን ዘወትር በራ ሰዓት ከጠዋቱ 3፡00-9፡00 ሰዓት ድረስ ማየት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት የመኪና ዓይነት /ሎት/ የጨረታ መነሻ ዋጋቸውን 10% /አሥር በመቶ/ የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO)"OMEDAD PLC”በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) በተጨማሪነት መኖር አለመኖሩን በመግለጽ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ፖስታ ጨረታው ከወጣበት 21ኛው ቀን ላይ እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ለሎቱ 100% መሆን አለበት፡፡
6. ጨረታው በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙት በቅሎቤት በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤት ይከፈታል።
7. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0114655467/0114669516/0930 03344 ደውለው ማግኘት ይችላሉ።
8. ኩባንያው ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ለመንግሥት የሚከፈለውን ስም ማዘዋወሪያ ይከፍላል።
10. አሸናፊው ድርጅት ወይም ግለሰብ ያሸነፈባቸውን መኪናዎች ክፍያውን ከፍሎ በ15 ቀናት ውስጥ ማንሳት አለበት።
ሞባይል 0911226853/0930033441
ስልክ ቁጥር 0114655467/0114669516
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ኦሜዳድ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ
