የቤት የሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
ሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት ሰላም ሆቴል የእቁብ ማህበር በፍ/ባለዕዳ 1ኛ አቶ በላይነህ ቢተው 2ኛ ወ/ሮ በተሀ ገድፍ 3ኛ ወለላው ጓዱ 4ኛ አበባው ታረቀኝ 5ኛ መንበር ጥላሁን 6ኛ እሱባለው ቦጋለ መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር ጉዳይ በአዲስ ቅዳም ከተማ 01 ቀበሌ የሚገኝ የ3ኛ የፍርድ ባለዕዳ ንብረት የሆነ አዋሣኙም በምስራቅ መንገድ፣ በምዕራብ ደሳለኝ ቆለጭ፣ በሰሜን አጋሉ የኔአባት፣ በደቡብ የወርቃየሁ ቤት፣ መካከል የሚገኝ ቤት፣ በመነሻ ዋጋ ብር 288,209.13/ሁለት መቶ ሰማኒያ ስምንት ሽህ ሁለት መቶ ዘጠኝ ብር ከአስራ ሶስት ሳንቲም/ ለሐምሌ 29 ቀን 2014 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 5፡00 በጨረታ ስለሚሸጥ መግዛት የሚፈልግ ሁሉ በቦታው ተገኝቶ መጫረት የሚችል መሆኑን ፍ/ቤቱ ያስታውቃል።
የአዊ ብሔ/ዞን/ከፍ/ፍቤት
