አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት የተለያየ መጠን ያለዉ የመለዋወጫ፣ ዲሲአይ ፓይፕ ፣ ጎማዎች ፣ የግንባታ ዕቃዎች፣ ቁርጥራጭ ብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
አማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት የተለያየ መጠን ያላቸው ያገለገሉ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። የተለያየ መጠን ያለዉ የመለዋወጫ፣ ዲሲአይ ፓይፕ፣ ጎማዎች፣ የግንባታ ዕቃዎች፣ ቁርጥራጭ ብረቶች፤
- ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለፁትን የጨረታ መወዳደሪያ መስፈርቶችን የሚያሟላ ማንኛውም ድርጅት በጨረታው መወዳደር ይችላል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚውልሲ.ፒ.ኦ ወይም ያለቅድመ ሁኔታ እንደተጠየቀ የሚከፈል ባንክ ጋራንቲ የጠቅላላ ዋጋዉን 10 በመቶ ብር ማስያዝ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ አሸናፊውን ተጫራች ድርጅት ወይም ግለሰብ በሚመርጥበት ጊዜ የሚሸጠውን የዕቃ መጠን እንደ አስፈላጊነቱ እስከ 50 በመቶ ሊቀንስ ወይም ሊጨምር ይችላል።
- ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሰዉን ዕቃ ባህርዳር ከተማ ከሚገኘው አስፋልት ፕላንት ግቢ በመቅረብ ማየት ይቻላል።
- ተጫራቾች መወዳደሪያ ሰነዳቸውን ማለትም ፋይናንሽያል ሰነድ አዘጋጅተው ባህርዳር ከተማ ከሚገኘው ዋና መ/ቤታችን አማራ መንገድ ስራዎች ድርጅት አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ፊት ለፊት የግዥ እና ንብረት አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው። ጨረታው በ15ኛ ቀን ከቀኑ 9:00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 9:30 ይከፈታል።
- በጨረታው ለተገለፁት እቃዎች ዝርዝር የጨረታ ሰነድ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከድርጅታችን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 23 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058-320-35-76 በመደወል ማብራሪያ መጠየቅ ይችላሉ።
የአማራ መንገድ ሥራዎች ድርጅት
