Tender Detail

Tender Details

  • Deadline05 Aug 2022, 12:37 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Accounting & Auditing

የቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብት እነ የውብነሽ አያሌው እና በፍ/ባለዕዳ እነ ሰለሞን አያሌው መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 299050 (22/6/2014 ዓ.ም እና በመ/ቁ 293609 ጥቅምት 22 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለውችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በልደታ |ከተማ ወረዳ 4 የቤ/ቁ 745 የሆነ ቤት የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 70,423.55 (ሰባ ሺ አራት መቶ ሃያ ሦስት ብር ከሃምሳ አምስት ሳንቲም) ብር የቦታ ስፋት በካርታ 99 ካ/ሜትር በ1988 የአየር ካርታ ላይ 96.25 ካሜትር ሬት ላይ የያዙት 99 ካ.ሜ የሆነ ቤቱ ካርታ ያለው ተጠቃቃሽ መዝገቦች ያለበት ሆኖ የትራንዛክሽን ታስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሀሴ 30 ቀን 2014 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት
በሚመርጧቸው ሦስት የሥራ ቀናት በፌ/ፍ|ቤቶች ፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ
ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በባን በተረጋገጠ C.PO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
በተጨማሪም ተጫራቾች ካፒታል ጌይን እና ታክስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ፣ ሐራጁ ጐድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬክቶሬቱ የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት

Save Tender