የኮንክሪት ፓምፕ ተሽከርካሪ ማሽን ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት ኢትዮ ክሬዲት ሲስተምስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና በፍ/ባለዕዳ አፍሮ ጽዮን ኮንስትራክሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 269607 በ25/10/2013 ዓ.ም. እና በመ/ቁ 265736 ሚያዚያ 12 ቀን 2013 ዓ.ም. በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ሮሆቦት የመኪና ማቆሚያ ግቢ የሚገኝ ኮንክሪት ፓምፕ ተሽከርካሪ ማሽን ላይ ያለ የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ዕዳ ብር 1,954,017.15 እና የቦሎ ዕዳ 446,000 ያለበት ሆኖ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 1,200,000 (አንድ ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ ብር ) ሆኖ ተጠቃቃሽ መዝገቦች ያሉበት ሆኖ ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 30 ቀን 2014 ዓ.ም. በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን ፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናት ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4ኛውን በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት።
በተጨማሪ ተጫራቾች ካፒታል ጌይን እና ታክስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ ፣ ሐራጁ ጎድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬክቶሬቱ የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን።
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ፍ/ቤት የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት
