ቶታል ኢነርጂስ ማርኬቲንግ ኢትዮጵያ አ.ማ. የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረቶችን እና ያገለገሉ ቆርቆሮዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረቶችን እና ያገለገሉ ቆርቆሮዎች ጨረታ
ቶታል ኢነርጂስ ማርኬቲንግ ኢትዮጵያ አ.ማ. የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረቶችን እና ያገለገሉ ቆርቆሮዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም ማንኛውም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ቅድመ ሁኔታዎች በሟሟላት መጫረት ይችላል።
- ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር የያዘውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- ዕቃዎቹን ጐተራ አካባቢ በሚገኘው የድርጅቱ ግቢ በመሄድ መመልከት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ላይ 10% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም C.P.O ከጨረታው ሰነድ ጋር ማስገባት አለባቸው። በጨረታው ለተሸነፉ ያስያዙት C.P.O ተመላሽ ይሆናል።
- ጨረታው ሐምሌ 4 ቀን 2014 ዓ.ም. ተከፍቶ ሐምሌ 19 ቀን 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ ይዘጋል።
- ተጫራቾች በሚያስገቡት ጠቅላላ ዋጋ ላይ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ መጨመር አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በፓስታ አሽገው ፓስታው ላይ የጨረታውን ስምና አድራሻቸው በመፃፍ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
- አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለፀለት ቀን አንስቶ በ 5 ቀን ውሰጥ ሙሉውን ዋጋ ከፍሎ ዕቃውን ካላነሳ ያስያዘው ገንዘብ በቅጣት መልክ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ አሸናፊነቱ ይሰረዛል።
- ቶታል ኢትዮጵያ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ከጎተራ ወደ ሳሪስ በሚወስደው መንገድ ላይ ቡና ቦርድ አካባቢ ሙለጌ ሕንፃ 7ኛ ፎ ላይ ነው።
ቶታል ኢነርጂስ ማርኬቲንግ ኢትዮጵያ አ.ማ.
