ኢትዮ ቴሌኮም በደቡብ ሪጅን ሀዋሳ አካባቢ እና በሪጅኑ ስር ላሉ አካባቢዎች የ2WD ፒካፕ (extended) እና ኩንታል የመጫን አቅም ያለው የካርጎ ትራክ የመኪና ክራይ አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል
የመኪና ኪራይ አገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
REQ NO. 4087229
ኢትዮ ቴሌኮም በደቡብ ሪጅን ሀዋሳ አካባቢ እና በሪጅኑ ስር ላሉ አካባቢዎች የ2WD ፒካፕ (extended) እና ኩንታል የመጫን አቅም ያለው የካርጎ ትራክ የመኪና ክራይ አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል። ስለዚህም የንግድ የመኪና ኪራይ ፈቃድ ያላችሁና ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ከደቡብ ሪጅን ኢትዮ ቴሌኮም ዋናው ጽ/ቤት አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 103 ሶርሲንግ ቢሮ በመቅረብ የማይመለስ 100 ብር ከፍለው ሰነዱን መግዛት ይችላሉ። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ28/11/2014 ዓ.ም ከቀኑ በ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ28/11/2014 ዓ.ም. ከከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ሶርሲንግ ቢሮ ይከፈታል።
መስፈርቶች፡
- የጨረታ ማስከበሪያ 30,000 ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፤
- የዘመኑን ግብር መክፈሉን የሚገልጽ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- የቲን ሰርተፍኬት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆኑን የሚገልፅ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- ተጫራቾች ፋይናንሻል እና ቴhኒካል ዶክመንት ዋናውንና ኮፒውን እንዲሁም ሲ.ፒ.ኦ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የድርጅት ባለቤትነት ማረጋገጫ በተዘጋጀው ቅጽ ላይ መፈረም ይኖርበታል።
- ከማጭበርበር / ከፀረ ሙስና ነፃ መሆኑን በተዘጋጀው ቅጽ ላይ መሙላት /መፈረም የሚችል።
ማሳሰቢያ፡-
መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ
የተጠበቀ ነው፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ሪጅን
