የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በአዲስ አባባ ከተማ ውስጥ ማዕከላዊ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ሕንፃ ኪራይ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥው መለያ ቁጥር:- አአከመባ/መደበኛ/ቡ2/002/2015
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን በአዲስ አባባ ከተማ ውስጥ ማዕከላዊ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ሕንፃ ኪራይ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መከራየት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
የሚፈለገው ቢሮ ስፋት በካሬ |
የጨረታ መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
የጨረታ ማስከበሪያ መጠን በብር |
||
|
1 |
ማዕከላዊ አዲስ አበባ የሪጅኑ ጂኦግራፊካል ማዕከል ከሆነበት ለገሀር ቤተዛታ ሆስፒታል አካባቢ አንፃራዊ መገኛ (472280.43, 995867.97) ከሚገኝበት ቦታ በ2 ኪ.ሜ. ራዲየስ ውስጥ የሚገኝ ህንፃ መሆን አለበት። |
ከ500-700 ካሬ
|
ሐምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም.
|
ከቀኑ 8:00
|
ሐምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም.
|
ከቀኑ 8:30
|
25,000.00
|
ስለዚህ፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፊኬት ፣ የግብር ከፋይ ሰርተፊኬት ፣ በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ ፣ አግባብነት ካለው የህግ አካል የተሰጠ በዘርፉ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት እንዲሁም በመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድህረ ገፅ (WWW.PPA.gov.et ) መመዝገብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ ብር 100.00(አንድ መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ መዝጊያ ተብሎ ከላይ እሰከተጠቀሰበት ቀን ድረስ ባሉት የሥራ ቀናት ከባለሥልጣኑ መ/ቤት የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 135 መውሰድ ይችላሉ።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ Certified payment (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የባንክ ዋስትና ከሆነ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bar Guarantee) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከባንክ የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ መሆን ይኖርበታል።
- ማንኛውም ተጫራች የመጫረቻ ሰነዱን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መዝጊያ ተብሎ እስከ ተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በባለሥልጣኑ መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 109 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባ አለባቸው።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከላይ በሰንጠረዡ የጨረታ መክፈቻ ተብሎ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት በባለሥልጣኑ ዋና መ/ቤት ይከፈታል።
ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ ስ.ቁ. ስልክ ቁጥር-011 372 2825/15/
ሳርቤት ፑሽኪን አደባባይ አካባቢ አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን
