Tender Detail

Tender Details

  • Deadline03 Aug 2022, 3:16 PM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Disposal Sale

ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


የጨረታ ማስታወቂያ

ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2014 አዲስ አበባ

ድርጅታችን ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ማንኛውም ድርጅትም ሆነ ግለሰብ በጨረታው ላይ መወዳደር ይችላሉ።

የጨረታ ዶክመንት ለመግዛት፡-

  1. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 250.00 (ሁለት መቶ ሃምሳ ብር) ብቻ በመክፈል ከሐምሌ 7 እስከ 22 ቀን 2014 ዓ.ም. በሥራ ሰዓት ከድርጅቱ ዋና መ/ቤት አዲስ አበባ መውሰድ ይችላሉ።
  2. ተጫራቾች ከሐምሌ 20-22 ቀን 2014 ዓ.ም. በስራ ሰዓት የሚሸጡትን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ጢያ ከተማ ከተማ ከኖክ ነዳጅ ማደያ ፊት ለፊት በሚገኘው የድርጅቱ ቅርንጫፍ ቢሮ ቅጥር ግቢ በመቅረብ መመልከት ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች ሊገዙት ለሚፈልጉት ተሽከርካሪዎች የሚያቀርቡትን ዋጋ በጨረታ ዶክመንቱ ውስጥ በተዘጋጀው የመጫረቻ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ አስገብተው ለዚሁ ጨረታ በድርጅቱ ዋና መ/ቤት አዲስ አበባ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከሐምሌ 25-27 ቀን 2014 ዓ.ም. የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪዎች የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 20% በወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ስም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ/ሲፒኦ/ ከጨረታው ሰነድ ጋር ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታው ሐምሌ 27 ቀን 2014 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በተከሰተው የCOVD-19 ወረርሽኝና መንግሥት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በብዛት መሰብሰብ በመከልከሉ ምክንያት በዚያው ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ከሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ኤጀንሲ በተገኙ ታዛቢዎችና ኤጀንሲው በሚመርጣቸው ውስን የተጫራቾች በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን አሸናፊው ወዲያውኑ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (ሲፒኦ) ታሳቢ በማድረግ ቀሪውን ገንዘብ በ10 ቀናት ውስጥ ከፍለው ንብረቱን የማንሳት ግዴታ አለባቸው።
  6. በጨረታ አሸንፈው ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ከፍለው ለማይወስዱ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል።
  7. ጨረታውን ያላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) የጨረታ አሸናፊው ከታወቀ በኋላ የሚመለስላቸው ይሆናል።
  8. ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ

ገርጂ አንበሳ ገራዥ አጠገብ

ስልክ ቁጥር፡- 011 629 3350/55/56/57

ፋክስ፡- 011 629 3346

ፖ.ሳ.ቁ.3330

አዲስ አበባ

 

 ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ

Save Tender