በኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ባ/ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የትራንስፖርት አገልግሎት ለመግዛት ስለሚፈለግ በዘርፍ ከተሰማሩ አካላት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ባ/ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት የትራንስፖርት አገልግሎት ለመግዛት ስለሚፈለግ በዘርፍ ከተሰማሩ አካላት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች መስፈርቶችና ግዴታዎች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
- የግብር መክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቢው ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ከታክስ ነፃ ለሆኑ አገልግሎቶች ተጨማሪ እሴት ታከስ መመዝገብ ታሳቢ ስለማይደረጉ በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋበዛሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 2% በጥሬ ገንዘብ ወይንም በባንክ በተመሰከረለት ቼ (C.PO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አንድ መቶ ብር በክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት በባህርዳር ከተማ ቀበሌ 03 አልካን ኮሌጅ ጎን ከሚገኘዉ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 305 በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መዉሰድ ይችላሉ፡ ፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሰነድ በጥንቃቄ በመሙላትና በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ፖስታ በማሸግና በዋጋ ሙያው ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በግልጽ በማስቀመጥ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ በ16ኛ ቀን ከጧቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በመስሪያ ቤቱ የግዥ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 307 ጧት 4፡30 ይከፈታል ነገር ግን 16 ኛው ቀን በዓል ፣ እሁድ/ ከሆነ 17 ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ 4፡30 ይከፈታል ፡፡
- የጨረታ አሸናፊው የመልካም ስራ አፈፃፀም ዋስትና 10% በጥሬ ገንዘብ ወይንም በባንክ በተመሰከረለት ቼ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንቲ የአመቱን በማስያዝ ከመ/ቤቱ ጋር ውል መፈራረም ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ በጨረታው የተገለፀውን አገልግሎት ብዛት እንዲገዛ አይገደድም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ ሙበቱ የተጠበቀ ነው
- ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን የንግድ መረጃዎችን ኦርጅናል ለብቻው አቅርበው ማሳየት ይኖርባቸዋል፡፡
- ለንግድ ስራ ፈቃድ መስጫ መመሪያ 17/2011 በኮድ 7112 የያዙት ሊብሬ የኪራይ ፈቃድ ያለው ወይም በንግድ ስራ ፈቃድ ኮድ 73 ዘርፍ የያዙት ሊብሬ የንግድ አገልግሎት የሚል እና በሊብሬውና በተወዳደረው ፈቃድ ስም የተጠቀሰው ታርጋ ብቻ መወዳደር የሚችል ሆኖ ሊብሬ ወይም የባለቤትነት ማረጋገጫ ወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በአንድ የጉዞ መስመር አንድ ሊብሬ ያለው ከሆነ አንድ መስመር ብቻ መሙላት ያለበት ሲሆን ሁለትና ከዚያ በላይ ሊብሬ ያለው ከሆነ እንደ ሊብሬው ብዛት የጉዞ መስመሩንም መሙላት ይቻላል፡፡ ነገር ግን አንድ ሊብሬ ኖሮት ከአንድ በላይ የጉዞ መስመር ከሞላ ሙሉ በሙሉ ውድቅ እንደሚደረግ ማወቅ አለበት፣ የሚሞላው የጉዞ መስመር እና ሊብሬው ብዛት ተመሳሳይ መሆን አለበት ማለት ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058-226-3401/058-320-1603
በኢትዮጵያ ገቢዎች ሚኒስቴር ባ/ዳር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
