ከአዲስ አበባ አሶሳ ነዳጅ ለማጓጓዝ የፈሳሽ ቦቴ ተሸከርካሪ ኪራይ አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
የፈሳሽ ቦቴ ኪራይ የትራንስፖርት
ተሽከርካሪ አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም
የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር EEU/BGREU/NCB/0022/2014
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽ/ቤት በያዘው በጀት ዓመት ለተቋሙ ነዳጅ ማደያ አገልግሎት ለመስጠት ከአዲስ አበባ አሶሳ ነዳጅ ለማጓጓዝ የፈሳሽ ቦቴ ተሸከርካሪ ኪራይ አገልግሎት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሰለሆነም ማንኛዉም በርፉ የተሠማሩ ግለሠብ ወይም ድርጅት መወዳደር የሚችሉ ሲሆን፤
በዚህ ጨረታ ላይ ለመሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
- ተጨራቾች የዘመኑን ግብር የከፋሉበትን የታደሠ የንግድ ፍቃድ የቫትና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ፤ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከ45 ሽህ እስከ 47 ሽህ ፈሳሽ ሊትር የሚይዝ ቦቴ መሆን ይኖርበታል፡
- ተጫራቾች በመንግስት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከትራንስፖርት ሚኒስተር የተሰጠዉ የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡
- የጨረታ ሰነዱን ይህ ማሰታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ hልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽ/ቤት በመቅረብ የማይመለስ ብር 400.00 / አራት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 / ሃያ ሽህ ብር/ ማስያዝ ያለባቸው ሲሆን EEU ASSOSA REGION ተከፋይ የሆነ ከታወቀ ባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም CPO ማስያዝ አለባቸው::
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸı ኢንቨሎፕ ኮፒና ኦርጅናል በማለት እስከ ተጠቀሰው የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት ድረስ በኢትዮጵያ ኤሌhትሪክ አገልግሎት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽ/ቤት አሶሳ ከተማ በራሱ ህንፃ 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 205 ድረስ በመቅረብ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 8:30 ላይ ይከፈታል፡፡
- ሪጅኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0572754844/0917834762/0917816560 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
አሶሳ ፤
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የቤኒሻንጉል
ጉሙዝ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጽ/ቤት
