የደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ለመግዛት ይፈልጋል
የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ለመግዛት የወጣ
ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 451/14
የደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ በህጻናት አድን ፕሮግራም ለታቀፉ ወረዳዎች በዓለም ምግብ ፕሮግራም /WFP / ጋር በመተባበር የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ላለባቸው በክልሉ በተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ በሚገኙ ቀበሌዎች ለማሰራጨት ለአንድ ዓመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::
|
ተ/ቁ |
የአገልግሎት ዓይነት |
የሚጓጓዝላቸው የምግብ መጠን |
የጨረታ ማስከበሪያ |
የጨረታ መክፈቻና ማሸጊያ |
||
|
በሜ/ቶን |
በካርቶን |
ማሸገያ |
መክፈቻ |
|||
|
1 |
የደረቅ ጭነት አገልግሎት |
861.314 |
240.083 |
20,000 |
9፡00 |
9፡30 |
በመሆኑም በንግድ ሥራ ዘርፉ የታደሰ ፈቃድ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸውና የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃዎች ያላቸውና የሚያቀርቡ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- የሚጓጓዘው ምግብ በ 61 ወረዳዎች በሚገኙ ቀበሌዎች ነው
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ለ60 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 20,000 ብር በሲ.ፒ .ኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ያስያዙበትን ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በቢሮው የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 2/11/2014 ዓ.ም ከቀኑ 9:00 ድረስ የማይመለስ ብር 100 በመከፈል በሀዋሣ ዩኒቨርሲቲ ጎዳና ከሚገኘው የመ/ቤቱ የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬhቶሬት ቢሮ ቁጥር 002 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነድ / ፕሮፎርማ/በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 2/11/2014 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ድረስ የቴክኒካልና ፋይናንሻል የመጫረቻ ሠነዶችን በአንድ ፖስታ በማዘጋጀት በቢሮው ግዥና/ንብ/አስ/ቢሮ ቁጥር 002 ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ቢሮው በቀረበው ጨረታ ላይ ካሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ከመፈራረሙ በፊት የግዥውን 20 ፐርሰንት መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል፡፡
- የጨረታው ሳጥን በ2/11/ 2014 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ታሽጐ በዕለቱ 9፡30 ሰዓት ተጫራቾች ተወካዮቻቸው/ በተገኙበት በቢሮው የግዥና /ንብ/አስ/ ቢሮ ቁጥር 002 ይከፈታል፡፡
- ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ 0462206596/0462125774 ይጠቀሙ::
በደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መንግስት ግብርና ቢሮ
