በቀጠሮ ማረፈያ ማዕከል /ቂሊንጦ/ ለአጠቃላይ ኮሚቴ ለህግ እስረኞች ለመዝናኛ ክበብ (ካፍቴሪያ) አገልግሎት የሚውል የተፈጨ ቡና ለአንድ አመት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በውል መግዛት ይፈልጋል
የጨረታ ማስታወቂያ
በቀጠሮ ማረፈያ ማዕከል /ቂሊንጦ/ ለአጠቃላይ ኮሚቴ ለህግ እስረኞች ለመዝናኛ ክበብ /ካፍቴሪያ/ አገልግሎት የሚውል የተፈጨ ቡና ለአንድ አመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በውል መግዛት ይፈልጋል፡፡
በጨረታው መሣተፍ የሚፈልጉ ሁሉ ከዚህ በታች የሚከተሉትን መመሪያና መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆኑን በዘርፉ የተሰማሩ ለሆናቸው በጀርባው የተገለፀ መሆን አለበት፡፡
- የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈለ የተጨማሪ እሴት ታhስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣
- የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉና የታደሰ የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው::
- የመንግስት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል አቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው ::
- ጥቃቅንና አነስተኛ ከሆኑ በጨረታው ለመሳተፍ ከአደራጃቸው አካል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፣
- የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 / አንድ መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር ስም በአካውንት ቁጥር 1000029497498 ገንዘቡን ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን ከግዥ ሥራ ከፍል ቢሮ ቁጥር 25 መግዛትይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶችና የዋጋ ማቅረቢያዎችን /ፋይናንሻል ሰነዶችን /በተለያዩ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ አለበት፡፡ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ በአንድ ላይ አሽጎ ያቀረበ ተወዳዳሪ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ጨረታው ውጭ ይደረጋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራቾች የሚያስገቡት ሰነድ ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናሉን እና ኮፒውን ለየብቻ እንዲሁም ፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናሉን እና ኮፒውን ለየብቻ በተለያዩ ፖስታ በማሽግ በፖስታው ላይ የሚጫረቱበትን የጨረታ ሰነድ ቁጥር በትhክል መፃፍ እንዲሁም በፖስታው ላይ እና በሁሉም የመጫረቻ ሰነድ ላይ የድርጅቱን ማህተም በመምታት ማስገባት ያለባቸው ሲሆን ስርዝ ድልዝ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የለውም::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያስይዙት ሲፒኦ ከቴክኒክ ሰነዶች ከኦርጅናሉ ጋር በአንድ ላይ አሽገው ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO በቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር ሥም አዘጋጅተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው በታሸገ ፖስታ እስከ ሰኔ 28 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 25 በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው እንዲሁም የባንከ ዋስትና የሚያስይዙ ተጫራቾች የቆይታ ጊዜው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር 90 ቀንና ከዚያ በላይ መሆን ይኖርበታል::
- ጨረታው ሰኔ 28 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 5፡30 ሰዓት ተጫራቾች/ወኪሎቻቸው/በተገኙበት ቂሊንጦ በሚገኘው በመ/ቤቱ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
- የጨረታው ዝርዝር መመሪያ በጨረታ ሰነዱ ተዘርዝሮ ቀርቧል:
- አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ማቅረብ ይቻልም እንዲሁም ዘግይተው የሚጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም::
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፈልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:
- ጨረታውን በሚከፈትበት ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
አድራሻ፤ ቀጠሮ/ ማረፊያ /ማዕከል/ አ/አ ሳይንስና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርስቲ አጠገብ
ለበለጠ መረጃ-011 471 63 33/011 888 60 89 ደውለው መጠየቅ ይቻላሉ::
ቀ/ማረ/ቤት አስተዳደር/ቂሊንጦ
