Tender Detail

Tender Details

  • Deadline18 Jul 2022, 11:09 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ለ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት) የፈርኒቸር ማምረቻ ግብዓቶች ግዥ (ለማህበረሰብ ት/ቤት) ፣ ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች ፣ ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች እና ኤልሲዲ ፕሮጀክተሮች ፣ የዋይት ቦርድ ማርከሮችና ዳስተሮች


የጨረታ ማስታወቂያ 

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ለ2015 ዓ.ም በጀት ዓመት) ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ግዥዎች መፈፀም ይፈልጋል፡-

  1. የፈርኒቸር ማምረቻ ግብዓቶች ግዥ (ለማህበረሰብ ት/ቤት)፣
  2. ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች ፣ላፕቶፕ ኮምፒውተሮች እና ኤልሲዲ ፕሮጀክተሮች ግዥ
  3. የዋይት ቦርድ ማርከሮችና ዳስተሮች ግዥ
  4. ለትሪትመንት ፕላንት (ዘመናዊ የቆሻሻ ማስወገጃ) አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን በማወዳደር ግዢ መፈጸም ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ሕጋዊ ሰነዶቻቸውን ከመወዳደሪያ የጨረታ ሰነድ ጋር፡

  • ሀ/ በዘመኑ የታደሰና በዘርፉ አግባብነት ያለው ህጋዊ የንግድ የሥራ ፍቃድ እና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣
  • ለ/ የግብር ከፋይነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት/TIN/፣
  • ሐ/ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣
  • መ/ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት ስለግብር አከፋፈል የሚገልጽ በጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የታhስ ከሊራንስ ማረጋገጫ፣
  • ሠ/ በመንግስት የዕቃና የአገልግሎት ግዢዎች ላይ ለመሳተፍ በመንግስት ግዢ ኤጀንሲ ድህረ ገጽ ላይ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፣
  • ረ/ በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ድርጅቶች 2014 ዓ.ም በጀት ዓመት የታደሰ የማይክሮ ኢንተርፕራይዝ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው ::
  1. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከታች በተገለጸው አድራሻ በዩኒቨርሲቲው ፕሮጀክት ፋይናንስ ክፍል ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ሕንጻ ቁጥር 106 ግዢና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 04 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. በተ.ቁ 1፣3 እና 4 ለተጠቀሱት እቃዎች ተጫራቾች አንድ የፋይናንስ ኦርጂናል እና አንድ የፋይናንስ ሰነድ ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ለተጠቀሰው የግዢ ዓይነት የጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አባሪ አድርገው የተጠየቁትን ማስረጃዎች በማሟላት የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በሁሉም ገጾች ላይ በማኖር ለፋይናንስ መወዳደሪያ ኦሪጂናልና ኮፒ ለየብቻ በማድረግ የታሸጉ ፖስታዎችን መመለስ ይኖርባቸዋል፡
  3. ተ.ቁ 2 ላይ ለተጠቀሱት እቃዎች አንድ የቴክኒክ ኦርጂናል አንድ የቴክኒክ ኮፒ እና አንድ የፋይናንስ ኦርጂናል እና የፋይናንስ ሰነድ ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ለተጠቀሱት የግዢ የጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አባሪ አድርገው የተጠየቁትን ማስረጃዎች በማሟላት የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በሁሉም ገጾች ላይ በማኖር ለቴክኒክ እና ለፋይናንስ መወዳደሪያ ኦሪጂናልና ኮፒ ለየብቻ በማድረግ የታሸጉ ፖስታዎችን መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተ.ቁ 1 እና 3 ላይ ለተጠቀሱት እቃዎች ተጫራቾች ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 (ሃያ ሺ ብር) እንዲሁም በተ.ቁ 2 እና 4 ላይ ለተጠቀሱት እቃዎች ተጫራቾች ለእያንዳንዳቸው የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ፣ ለ90 ቀናት የሚቆይ የባንክ ዋስትና (ጋራንቲ) በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስም አዘጋጅተው ወይንም በጥሬ ገንዘብ ለዩኒቨርስቲው ፋይናንስ በመክፈል ከጨረታ ሰነዱ ጋር አባሪ አድርገው በተሰጠው ስፔስፊኬሽን ላይ በመሙላትና የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ በሁሉም ገጾች ላይ በማኖር ኦሪጂናል እና ኮፒ ፖስታዎችን በሰም በታሸገ በተለያዩ ፖስታ በማድረግ መመለስ ይኖርባቸዋል፡፡
  5. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በ16ኛው ወይም በ17ኛው ተከታታይ ካላንደር ቀን የሚከፈት ይሆናል (በጨረታ ሰነድ የመጀመሪያው ገጽ ላይ ይመልከቱ)፡፡ ተጫራቾች የመወዳደሪያ የጨረታ ሰነዱን ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው ይፋ ከተደረገበት ዕለት ጀምሮ ጨረታው እስከሚታሸግበት ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ መመለስ ወይንም ማስገባት ይችላሉ፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት 16ኛው ወይም 17ኛው ካላንደር ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የሕዝብ ባዕላት ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ነው፡፡
  6. ዝርዝር መረጃውን በተመለከተ ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ገዝተው ማየት ይችላሉ፡፡ ዩኒቨርሲቲው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡:

ለተጨማሪ ማብራሪያ የዩኒቨርሲቲው ድረ ገጽ www.astu.edu.et እና መንግስት ግዥ ኤጀንሲ ድረ ገፅ በመጎብኘት የጨረታውን ዝርዝር መመልከት ይችላሉ፡፡

በተጨማሪም በስልክ ቁጥር 022 211 0003/022 211 0094 ደውሎ በመጠየቅ አስፈላጊውን መረጃ ማግሰኘት ይችላሉ፡፡

አዳማ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ 

Save Tender