Tender Detail

Tender Details

  • Deadline13 Jul 2022, 10:47 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure

የቡራዩ ከተማ አስተዳደር የጋራ መኖሪያ ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።


ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የቡራዩ ከተማ አስተዳደር በ2000 ዓመተ ምህረት ግንባታቸው ተጀምሮ የግንባታ ደረጃቸው80% በታች የሆኑ የጋራ መኖሪያ ቤት ብዛት 1 /አንድ/ ብሎክ/ህንጻ 14 በገፈርሳ ኖኖ ቀበሌ ከሻቃ ወደ ቡራዩ ማዘጋጃ ቤት በሚወስድ መንገድ ላይ በተለምዶ አሸዋ ሜዳ ተብሎ በሚጠራ አከባቢ ያለ ቤት አሁን ባለበት ደረጃ ላይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት የምታሟሉ መወዳደር ትችላላችሁ፡፡ ቤቱ የሚገኝበት በቡራዩ ከተማ አስተዳደር በገፈርሳ ኖኖ ቀበሌ ከሻቃ ሞል ልዩ ስሙ አሸዋ ሜዳ ኮንዶሚንየም በሚባል አካባቢ ነው፡፡

  1. ተጫራች ቤቱ የሚገኝበትን ደረጃ በቦታው በአካል በመገኘት ማየት ይችላል፡፡
  2. ለጫረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ 50,000 ብር በሲፒኦ /በቼክ ማስያዝ የሚችልና ጨረታውን ካሸነፈ ለውል ማስከበሪያ ያሸነፈበት ቤት ጠቅላላ ዋጋ ከፍሎ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ መውሰድ ይችላል፡፡
  3. . ተጫራቹ ጨረታውን ካሸነፈ ቤቶቹን በራሱ ወጪ የቀረውን ግንባታ ይጨርሳል፡፡
  4. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናቶች በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው ቀን 8:30 ሰዓት ላይ የሚዘጋ ሲሆን በዚሁ ቀን በ9:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ተወካዮቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል::
  5.  ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በማይመለስ 250 ብር ከቡራዩ ከተማ ገ/ኢ/ትብብር/ጽ/ ቤት ቢሮ ቁጥር 107 መግዛት ይችላሉ፡፡
  6.  በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚችሉት ግለሰቦች፤ጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጅቶችና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

ማሳሰቢያ፡* መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቡራዩ ከተማ አስተዳደር የገንዘብና የኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት 

 

Save Tender