በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የገቢዎች ሚኒስቴር በታክስ ዕዳ የያዛቸውን ንብረቶች ለመሸጥ ይፈልጋል።
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የገቢዎች ሚኒስቴር በታክስ ዕዳ የያዛቸውን ንብረቶች ለመሸጥ የወጣ ግልጽ የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ ቁ-10/2014
የሚኒስቴር መ/ቤቱ በታክስ ህጉ መሰረት በተቀመጠው ጊዜ የሚጠበቅባቸውን የታክስ ዕዳ ባለመክፈላቸው ምክንያት የተያዙ የኦክስፎርድ አማልጌትድ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የጥጥ መዳመጫና መፍተያ ማሽን ፣ የማደበሪያ ክር ማምረቻ ማሸን የስፌት ማሽኖች እና የማሽኑ መለዋወጫዎች (spare parts) የካልወርክ ኢትዮጵያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከአልሙኒየም የተዘጋጁ የብረት ድስቶች ማንቆርቆሪያ የማንቆርቆሪያ ማንጠልጠያና የተለያየ ሞዴል ያላቸው ተሽከርካሪዎች ንብረትነታቸው በሀይቅ ጠ/ንግድ ኢንቨስትመንት፣ታግ ኮንስትራክሽን፣ የሪትም የወተት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግ/ማህበር፣የታኮ ኮንስትራክሽን ሎጅስቲክስ እና ትሬዲንግ፣ኽርበር ፋርማሲዩቲካልስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር፣የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቢዝነስ ኢንተርፕራይዝ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና ኢኖቫ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የ7 ድርጅቶች 7 ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም:
1.በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች ማንነቱን የሚገልጽ የነዋሪነት (ፖስፖርት) መታወቂያ ጨምሮ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለግልፅ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል
2 ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ የግልፅ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋትን ጨምሮ ከ2፡00-6፡00 ሰዓት ህንፃ “መ” 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ከግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ህንፃ “ሀ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 202 በታክስ ዕዳ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ መውሰድ ይኖርባቸዋል፡
3. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ንብረቶች (ለጨረታው መለያ ኮድ) የሰጡትን ዋጋ 1/10ኛውን ብቻ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) በገቢዎች ሚኒስቴር ስም (Ministry of Revenue) በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት ሰነድ ገዝተው መጫረት ይችላሉ።
|
ተ.ቁ |
የመ/ቤቱ ስም |
ለጨረታ የቀረበው የንብረት ዓይነት |
የንብረቶቹ መመልከቻ ቀን
|
የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
1 |
ገቢዎች ሚኒስቴር
|
1. ከአልሙኒየም የተዘጋጁ የብረት ድስቶች፣ ማንቆርቆሪያ የማንቆርቆሪያ ማንጠልጠያ 2. የተለያየ ሞዴል ያላቸው ተሽከርካሪዎችና 3. የጥጥ መዳመጫ መፍተያ ማሽን፣ የማዳበሪያ ክር ማምረቻ ማሽን የስፌት ማሽኖች እና የማሽን መለዋወጫ(spare part) |
ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት
|
ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 15 ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ቀጥሎ ባለው 16ኛ ቀን 3፡45 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡00 ሰዓት ይከፈታል |
5. የጨረታ መክፈቻ ቦታ- መገናኛ በሚገኘው በሚኒስቴር መ/ቤቱ ህንፃ “መ” 6ኛ ፎቅ ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት/ ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል ።
6. የግልፅ ጨረታው መክፈቻና መዝጊያ 16ኛው ቀን የመ/ቤቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን የግልፅ ጨረታው መክፈቻና መዝጊያ ቀን ይሆናል ።
7. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር እንደአስፈላጊነቱ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የግልፅ ጨረታ ኮሚቴው መረጃውን አጣርቶ እንደጨረሰ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል
8. የተሽከርካሪ ጨረታ ለሚያሸንፉ ተጫራቾች ከስመ ንብረት ዝውውር ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ወጪዎች (የቦሎና ሌሎች ተጓዳኝ ወጪዎች) ሻጭን አይመለከትም
9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ መ/ቤቱ በሚሰጠው አድራሻ ገቢ በማድረግ ያሸነፉበትን ሀብት/ንብረት መረከብ ይኖርባቸዋል፡፡
10. ከላይ በተ/ቁ 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ በማድረግ ንብረታቸውን ያልተረከቡ ተጫራቾች የግልፅ ጨረታው ተሠርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት የዋስትና ገንዘብ ለሚኒስቴር መ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ንብረቱ እንዳልተሸጠ ተቆጥሮ በቀጣይ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።
10. ሚኒስቴር መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ የግልፅ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-617-8490 ኮድ(2044)(2045) (2046) የውስጥ መስመር (EXT) 2044 ደውለው መጠየቅ ወይም የተቋሙን ዌብሳይት WWW.MOR.Gov.et መመልከት ይቻላል::
ገቢዎች ሚኒስቴር
