Tender Detail

Tender Details

  • Deadline25 Aug 2022, 10:34 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure

የቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ


የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

በፍ/ባለመብት እነ አቶ ካሳ ብርቅነህ እና በፍ/ባለዕዳ እነ ወ/ት ሸዋዬ ተስፋዬ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 143228 30/5/2008፤87684 ህዳር 20 ቀን 2008 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በየካ /ከተማ ወረዳ 10 አንቆርጫ ገ/ማህበር የቤ.ቁ የሌለው በአዋሳኝ በሰሜን መንገድ በምስራቅ ወ/ሮ ሳራ አብርሀም በምዕራብ ወ/ሮ መገርቱ አንበሴ በደቡብ እነ ከፍአለ የሚያዋስኑትን ቤት የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 305,240(ሶስት መቶ አምስት ሺ ሁለት መቶ አርባ ብር ) ስፋቱ 200 ካ.ሜ ሠነድ አልባ ካርታ ያልወጣለት ካርታ ፕሮሰስ ላይ ያለመሆኑ ታውቆ ሆኖ የትራንዛክሽን ታከስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሀሴ 19 ቀን 2014 በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ በ5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቁ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለብቱ ለማስጎብኘት በሚርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬከቶሬት ሐራጅ ከፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል 1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም:: በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡

በተጨማሪ ተጫራቾች ካፒታል ጌይን እና ታከስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ፣ ሐራጁ ጐድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬክቶሬት የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት

 

 

Save Tender