Tender Detail

Tender Details

  • Deadline07 Jul 2022, 9:56 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Sales, Disposals And Foreclosure

የተቀናጀ የቤተሰብ አገልግሎት ድርጅት ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።


በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ድርጅታችን ሲገለገልባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ ቀደም ብሎ የሰጠውን መነሻ ዋጋ በማስተካከል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም፡-

  1. ማንኛውም ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ንብረቶቹ በሚገኙበት አድራሻ ማለትም ሾላ ገበያ ወደ ሲግናል በሚወስደው መንገድ የትራፊክ መብራቱን ሳይሻገር ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ቤክማ ዳቦ ቤት አጠገብ በሚገኘው በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ግቢ ውስት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 7፡30 ሰዓት ድረስ መመልከት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረት ጠቅላላ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) አሰርተው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ለአሸናፊዎች ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን፤ ለተሸናፊዎች የጨረታው ውጤት በፀደቀ በ3/ሦስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ይመለስላቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች የንብረቶቹን ዝርዝር የያዘው ሰነድ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ (Column) ስር የሚገዙትን ዋጋ በአሃዝና በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልጸው በታሸገ ኤንቨሎፕ (ፖስታ) ድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ነገር ግን የሚሰጡት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ከጎኑ በተጫራቹ መፈረም አለበት፡፡
  5. ተጫራቾች ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሰነድ ማስገባት አለባቸው፡፡ በአስረኛው ቀን ግን የጨረታ ሰነዱ የሚገባው እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡
  6. አሸናፊ ተጫራጮች ጨረታውን ማሸነፋቸውን ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ ከ3-5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ገቢ በማድረግ በ10/አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ተሽከርካሪውን የመረከብ ግዴታ አለባቸው ይህ ካልሆነ ያስዙት ገንዘብ ወይም ሲፖኦ ለድርጅቱ ገቢ ይሆናል፡፡
  7. ተጫራቾች ከድርጅቱ አስተዳደር ክፍል የተሽከርካሪዎችን ዝርዝር መረጃ የያዘ የተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ብር 100.00/አንድ መቶ ብር/ እየከፈሉ ማስታወቂያው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናቶች ድረስ መግዛት የሚችሉ ሲሆን፤ በአስረኛው ቀን ግን ሰነዱ የሚሸጠው እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይሆናል፡፡
  8. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ የሥራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ10ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን 4፡30 ተጫራቾቹ ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ ዋና መ/ቤት ይከፈታል፡፡

ተጫራቾች ስለአሻሻጡ ዝርዝር ሁኔታ ከጨረታው ሰነዱ ጋር ከተያያዘው የተጫራቾች መመሪያ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ድርጅቱ ለአሻሻጡ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለጨረታ የሚቀርቡት ተሽከርካሪዎች፡-

  1. Toyota Land Cruiser 4WD (ላንድ ክሩሰር 1HZ Engine)
  2. Toyota Runner 4WD (ራነር) ናቸው፡፡

ለበለጠ ማብራሪያ

  • በስልክ ቁጥር 093 386 6459፣ 0911 43 37 07፣ 011 869 97 25፣ 0920 04 39 13  እና 011 812 2773 መደወል ይቻላል፡፡

የተቀናጀ የቤተሰብ አገልግሎት ድርጅት

Company Info
Save Tender