የቤት የሐራጅ ሽያጭ
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት ወ/ሮ ኤደን አድማሱ እና በፍ/ባለዕዳ አቶ ሳሙኤል አሰፋ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/96930፤123417በ29/03/2013 እና በ30/06/2013 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 10 አያት ቁጥር አንድ ብሎክ 68 የቤት ቁጥር BAB-B68/12AA000061007330680212 በአቶ ሳሙኤል አሰፋ ስም የተመዘገበ ካርታ ያለው ስፋቱ 45.44 ካ/ሜ የሆነ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 276,240 (ሁለት መቶ ሰባ ስድስት ሺ ሁለት መቶ አርባ ብር) የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሐምሌ 29 ቀን 2014 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ 8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤ እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡
በተጨማሪ ተጫራቾች ካፒታል ጌይን እና ታከስ ስምን ይዛወርልኝ የሚልን ጥያቄ፣ ሐራጁ ጐድቶኛል የሚሉ ጥያቄዎችን ዳይሬክቶሬቱ የማያስተናግድና በችሎት የሚጠየቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት
