Tender Detail

Tender Details

  • Company በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251112730852
  • Websitehttps://www.fsc.gov.et/
  • Deadline28 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየንብረቱ ግምት 1/4ኛ ብር 4,140,195 (C.P.O)
  • opening dateምዝገባው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ፣ በፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ
  • Sector Foreclosure , House and Building Foreclosure , House and Building , House and Building Sale

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት በጉለሌ ክ/ከተማ የሚገኝ የውርስ ይዞታ ሐራጅ ሽያጭ

በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት

Add to calendar Google Calendar Download .ics

ድጋሚ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

የፍ/ባለመብት ተማሪ ማህሌት ሀይሉ እና በፍ/ባለዕዳ እነ አቶ ብርሃኑ አስታጥቄ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 77432 በ21/4/2013 ዓ/ም በ23/12/2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ እና በኮ/መ/ቁ/88696 በ11/9/2014ዓ.ም መሠረት በጉለሌ /ክ/ከተማ ወረዳ 01 የቤት ቁጥር 753 የሆነው የሟች አስታጥቄ ወ/አምላክ እና የሟች ወ/ሮ አስናቀች ንጋቱ የውርስ ይዞታ በካ/ቁ/19/11/30807/01 በእነ አቶ በርሃኑ አስታጥቄ ስም የተመዘገበ የቦታው ስፋት 585 ካ/ሜ ሲሆን ከአጠቃላይ ይዞታው በስትራክቸራል ፕላን መሰረት 130 ካ/ሜ መንገድ የሚነካው የሆነ የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 16,560,780 (አስራ ስድስት ሚሊዮን አምስት መቶ ስልሳ ሺህ ሰባት መቶ ሰማኒያ ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሚያዚያ 21 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ለመሸጥ ቀጠሮ የተያዘ ቢሆንም በዕለቱ ተጫራች ባለመቅረቡ ምክንያት ጨረታው ሳይከናወን ቀርቷል:: ስለሆነም በፌ/መ/ደ/ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ.88696 በቀን 25/02/2019 ዓ.ም በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በድጋሚ ሐራጅ ጨረታ ሆኖ 1/4ኛ ብር 4,140,195 ( አራት ሚሊዮን አንድ መቶ አርባ ሺህ አንድ መቶ ዘጠና አምስት ብር) በማስያዝ መሳተፍ የሚቻል ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ታህሳስ 19 ቀን 2019 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል::የተጫራቾች ምዝገባ 4:00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያዉኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል:: የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3:30 ጀምሮ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ መጎብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን ግምት 1/4 ኛውን በኢትጵዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ c.P.O ማስያዝ ይኖርበታል:: ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ CPO የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም:: በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አ/ጽ/ቤት C.P.O አሰርተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተከፈተ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታው አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳያደርግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታ ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሀራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመፃፍ ባለፈ ስም የማዘወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን:: ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +25112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን::

የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት

Summary
Federal Courts Judgment Execution Office re-auctions an inherited residential property on a 585 sq.m plot in Gulele Sub-City, Woreda 01, Addis Ababa, by court order.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender