የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (ትራንስሚሽን ቢዝነስ) የእርዚንግ ሲስተም ዕቃዎች (የኮፐር ኮንዳክተር እና እርዚንግ ሮድ) አቅርቦት ግዢ ያወጣው ሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ (ቁጥር EEP/TBP/NCB/03/2019)።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power)
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር EEP/TBP/NCB/03/2019
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከዚህ በታች በሰንጠረዥ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች አቅርቦት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ድረ-ገጽ ላይ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ በስራ ሰዓት የካ ክ/ከ ወረዳ 9 ኮተቤ ብረታ ብረት ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና መ/ቤት ህንፃ ቁጥር-11 2ኛ ፎቅ በሚገኘው ገንዘብ ተቀባይ ቢሮ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ) በመክፈል ወይም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በEEP Transmission Substation Construction Account No.1000252665203 ገቢ በማድረግ የጨረታ ሰነዱን ህንፃ ቁጥር-19 ትራንስሚሽን ቢዝነስ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 114 በመምጣት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጹትን ዕቃዎች አቅርቦት ግዥ በሚመለከት የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ዝርዝር በታሸገ ኤንቬሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/TBP/NCB/03/2019 የሚል ምልክት በማድረግ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ተጫራቾች ከዚህ በታች በተዘረዘረው ዕቃ አቅርቦት ግዥ መወዳደር ይችላሉ፡፡
| የዕቃዎች አቅርቦት ግዥው ዓይነት | የጨረታ ማስከበሪያ | የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት | የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|---|---|---|---|
| የእርዚንግ ሲስተም/ Earthing system materials (ኮፐር ኮንዳክተር እና እርዚንግ ሮድ) ዕቃዎች አቅርቦት ግዥ | ብር 500,000.00 | ታህሳስ 06 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት | ታህሳስ 06 ቀን 2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:15 ሰዓት |
ግዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0116732190 መደወል ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
Summary
Ethiopian Electric Power (Transmission Business) buys earthing system materials, copper conductor and earthing rods, through national open bidding. Bidders need a renewed licence, VAT and registration on the procurement agency supplier list.
