Tender Detail

Tender Details


የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ለእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር አገልግሎት የአጭር ስልክ መስመር PVX ሥርዓት ግዢ ያወጣው ግልጽ ጨረታ።

Hawassa City Administration

Add to calendar Google Calendar Download .ics

የጨረታ ማስታወቂያ

የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋ/ኢ/ል/መምሪያ ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በ2019 በጀት ዓመት በታቀደው መሠረት ለእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር አገልግሎት አጭር ስልክ መስመር PVX ግዥ ለመፈጸም በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው ድርጅቶች መካከል በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡-

  1. በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣
  2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና
  3. የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
  4. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
  5. በጨረታው እንዲሳተፍ የታክስ ክሊራንስ ማቅረብ አለበት፣
  6. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋ/ኢኮ/ልማት መምሪያ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 /አስር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሰነድ በብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመግዛት ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለበት፡፡
  8. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል አሟልቶ በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10(አስር) ተከታታይ ቀናት በፋ/ኢኮ/ልማት/ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. አስፈላጊ የሆኑ ቴክኒካል ጉዳዮች በሚሸጥ ሰነድ ውስጥ በተቀመጠው መስፈርት መሠረት የሚገመገም ስለሆነ በጥንቃቄ መዘጋጀት ይጠበቅበታል፡፡
  10. የሚገዙት እቃዎች እስቶክ ውስጥ መኖራቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ማቅረብ አለበት (እስቶክ ውስጥ መኖሩ ግዴታ ነው)፡፡
  11. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት፣ ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈትበት ቀን ይሆናል፡፡ የበዓል ቀን ከሆነ ደግሞ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
  12. በጨረታ ማስታወቂያ እና በጨረታ ሰነድ ላይ የሚጣረዝ ሁኔታ ካለ፣ የጨረታ ሰነዱ በላይነት ይኖረዋል፡፡
  13. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ስልክ ቁጥር፡- 046-212-13-34

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና /ኢኮ/ል/መም/ያ

Summary
Hawassa City Administration Finance and Economic Development Department buys a short-code telephone line PVX system for the city fire and emergency prevention and control service. Licensed suppliers must prove the goods are in stock.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender