የወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የስልጠና፣ የቢሮ፣ የጽህፈት፣ የኮንስትራክሽንና የአይሲቲ ዕቃዎች ግዥ
Wolaita Sodo PolyTechnic (የወላይታ ሶዶ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የወላይታ ሶዶ ፖሊ. ቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 ዓ.ም አንደኛ ዙር የተለያዩ የስልጠና ዕቃዎችን እና ሌሎች ዕቃዎችን በመደበኛና በካፒታል በጀት ለመግዛት ማለትም:-
- አግሮ ፕሮሰሲንግ ዕቃ
- አውቶሞቲቭ ዕቃ
- ብረታ ብረት
- የቤትና ቢሮ/ፈርኒቸር ዕቃዎች
- የጽህፈት መሣርያዎችና የጽዳት ዕቃዎችን
- የኮንስትራክሽን ዕቃዎች
- ጋርመንትና ሌዘር
- ደንብ ልብስ
- ሆቴል
- B. I. E
- ኤሌክትሪክ ቴክኖሎጅ
- አይ.ሲቲ/የኮሚፒተር ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች:-
- የዘመኑን የታደሰ የንግድ ፈቃድና የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- የግብር ከፋይነት መለያ VAT ሰርተፍኬት ያለው
- በአቅራቢነት የተመዘገበበትን መረጃ/የድረ-ገጽ ምዝገባ ሰነድ ማቅረብ የሚችል
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የዘመኑን የግብር ግዴታዎችን ስለመወጣታቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ሆኖ ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሰረት ማለትም:-
- የእያንዳንዱን ጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር /ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ወላይታ ሶዶ ፖሊ. ቴ/ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 104 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን በመግዛትና ኮሌጁ ባዘጋጀው ጨረታ ሰነድ ሞልተው በማስገባት መወዳደር ይቻላል።
- የጨረታውን ሰነድ በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦርጅናልና በ1 ኮፒ በጨረታ ሳጥኑ መጨመር ያለበት ሲሆን ከአንድ በላይ የጨረታ ሰነድ የሚገዙ ድርጅቶች ሲፒኦን በጥቅል ማድረግ ሲችሉ ሌሎች ሰነዶችን በእያንዳንዱ ፖስታ ውስጥ ከጨረታ ሰነድ ጋር ካላሸጉ ከጨረታው ውጪ ይደረጋሉ።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዕቃዎች ጠቅላላ ዋጋ 1% የጨረታ ማስከበሪያ በማስላት በባንክ የተረጋገጠ ቼክ፣ ጋራንት እና ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። የጠቅላላ ዋጋ ከ1% በታች የሚያስገቡ ተጫራቾች ከጨረታ ውጪ ይደረጋሉ። አሸናፊዎች በቅድሚያ 10% ውል በመግባት የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ፣ጋራንትና ሲፒኦ በማስያዝ ውል ይገባሉ። አሸናፊ ድርጅቶች ውል ለመግባት ፈቃደኛ ካልሆኑ የጨረታ ማስከበሪያው ውርስ ይደረጋል። ኮሌጁ ከአሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉትን ዕቃ የሚረከበው ውል ከገቡበት ቀን ጀምሮ በኮሌጁ ግቢ ብቻ ስለሆነ ጨረታውን የሚያሸንፉ ድርጅቶች ያሸነፉትን ሙሉ ዕቃ እስከ ኮሌጁ ግቢ በማምጣት የሚያስረክቡ ይሆናሉ። የዕቃዎቹም ጥራትና ዓይነት በኮሌጁ ባለሙያዎች ተረጋግጦ ተቀባይነት ካላገኘ ኮሌጁ ለመረከብ አይገደድም።
- ጨረታው የሚታሸግበት ቀንና ቦታ:- ሶዶ ፖሊ. ቴክኒክ ኮሌጅ ግቢ ሲሆን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 10:30 ሰዓት ሲሆን 15 ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።
- የሚከፈትበት ቀንና ቦታ ወላይታ ሶዶ ፖሊ.ቴክኒክ ኮሌጅ ግቢ የጨረታ ሰነዱ ተሽጦ በተጠናቀቀበት በ2 ኛው የስራ ቀን ከቀኑ በ4:00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተሸናፊ ድርጅቶች ያስያዙት ቼክና ሲፒኦ ይመለስላቸዋል።
- በጨረታ ሰነድ ላይ የተገለጸውን ስፔስፒከሽን መቀየርና መደለዝ እንዲሁም የተደለዘ የተጫራች ሰነድ ተጫራቾችን ከጨረታው ውጪ ያደርጋቸዋል።
- ድርጅቶች ተገቢውን አድራሻ ማህተም ስልክ እና የፋክስ ቁጥርን ጨምሮ በሰነዱ መግለጽ ይኖርባቸዋል።
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር / 0912111340 /0913302499/ 0916715114 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የወላይታ ሶዶ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ /ወላይታ ሶዶ/
Summary
Wolaita Sodo Polytechnic College invites bids for training and other items including agro-processing, automotive, metal, furniture, stationery, cleaning, construction, garment, uniforms, hotel, electrical and ICT items.
