የዳሎቻ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የስልጠና ማቴሪያሎች፣ ቋሚና አላቂ ዕቃዎች ግዥ
Dalocha Poly Technic College (ዳሎቻ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ)
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢ.ት/ ክል /መንግስት የስራ እና ክህሎት ቢሮ ስልጤ ዞን ዳሎቻ ፖ.ሊ. ቴክኒክ ኮሌጅ በ2019 በጀት ዓመት ለቢሮና ለስልጠና ክፍሎች አገልግሎት የሚውል የስልጠና ማቴሪያል የተለያዩ ቋሚእና አላቂ ዕቃዎችን በሚዲያ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል ::
- የአውቶሞቲቭ ማቴሪያሎች
- ለቧንቧና ለፍሳሽ ስራዎች የሚያገለግሉ ዕቃዎች
- የተለያዩ ብረታ ብረቶችና ላሜራዎች
- የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልዩ ልዩ ዕቃዎች እና መለዋወጫዎች
- ለህንጻ ኤሌክትሪክ ዝርጋታ የሚያስፈልጉ ልዩ ልዩ የስልጠና ዕቃዎች እና መለዋወጫዎች
- ጋርመንት የስልጠና ማቴሪያል
- የኮንስትራክሽን የተለያዩ ዓይነት ዕቃዎች እና መለዋወጫዎች
- ሆቴል ቱሪዝም ማሽነሪዎች እና ቋሚ የስልጠና ማቴሬያል
- የቢሮ አላዊ ዕቃዎች
- የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የግብር ከፋይነት መሰያ ቁጥር የምዝገባ ሰርተፊኬት የሚያቀርቡ
- ከሚያቀርቡት ጠቅላላው ዋጋ የጨረታ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ሶ ማስያዝ የሚችሉ
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት እያንዳንዱ ሰነድ ላይ ፊርማቸውንና የድርጅቱን ማህተም ማኖር ይጠበቅባቸዋል::
- አሸናፊው ተጫራች ውል ከገባበት ቀን ጀምሮ ዕቃዎችን በ15 ቀናት ውስጥ በኮሌጁ ማስረከብ ይጠበቅበታል::
- ሌሎች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም
- ተጫራቾች የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኤጀንሲ ያወጣውን ደረጃ መሰረት በማድረግ ባቀረበው የዋጋ ዝርዝር ሰነድ ውስጥ የተገለፁ እቃዎች /ማሽኖች/ በወጣው ስታንዳርድ መሰረት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው
- ከላይ ከተራ ቁጥር 1-7 የተገለፁትን ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች ሰነዱን ከኮሌጁ ግዢ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የስራ ሂደት ቢሮ በመቅረብ ለሰነዱ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ብቻ በባንክ አካውንት በመክፈል መግዛት የሚችሉ መሆኑን እያሳወቅን የጨረታ ሰነዱን በአግባቡ በመሙላት አንድ ኦርጂናል እና አንድ ኮፒ ብቻ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15/አስራ አምስት/ ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባለው የስራ ቀን 9:00 ሰዓት ድረስ በኮሌጁ ግ/ፋ/ን/አስ/ር የስራ ሂደት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው ሣጥን ከላይ በተራ ቁጥር 8 ላይ በተገለፀው ዕለት 9:00 ሰአት ታሽጎ ከቀኑ 9:30 ሰዓት ላይ በመገኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ማሳሰቢያ
- ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ካቀረቡት ዋጋ አንሶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛሉ
- የተወዳዳሪዎች ወይም የህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታውን መከፈቻ ቀን አይለውጥም
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
ለበለጠ መረጃ:- በስልክ ቁጥር 0928823101 / 0983662404 /ይደውሉ
በስልጤ ዞን የዳሎቻ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
Summary
Dalocha Polytechnic College invites bids for training materials and office items including automotive, plumbing, metal, IT, electrical, garment, construction, hotel and tourism, and office consumables.
