ዋልታ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን (ቡታጅራ) የ2019/20 ምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ ዳፕና ዩሪያ ከቡታጅራ ማዕከላዊ መጋዘን ወደ ምስራቅ ጉራጌ ዞን ወረዳዎች ማራገፊያ ጣቢያዎች ለማጓጓዝ ለመጀመሪያ ጊዜ ያወጣው የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ጨረታ (ቁጥር ዋገዩ 001/2019)።
ዋልታ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ኃላ.የተወሰነ
የአፈር ማዳበሪያ ለማጓጓዝ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ጨረታ ቁጥር ዋገዩ 001/2019
ዋልታ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ጉራጌ ዞን ስር በሚገኙ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም በማረቆ ልዩ ወረዳ ውስጥ ላሉ አርሶ አደሮች በያዝነው በ2019/20 ምርት ዘመን በ ቡታጅራ ከተማ ከሚገኘው ማእከላዊ መጋዘን ወደ ማራገፊያ ጣቢያዎች በበልግና በመኸር ዳፕ እና ዩሪያ የአፈር ማዳበሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከዋልታ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን በእያንዳንዱ ወረዳ የሚገኙ የማራገፊያ ጣቢያዎችን ዝርዝር መግለጫ በመውሰድ ለማጓጓዝ የሚፈልገውን የማድረሻ ዋጋ በጠጠርና በአስፋልት መንገድ በአማካኝ በኩንታል በአንድ ኪሎ ሜትር ተሰልቶ በእያንዳንዱ ጣቢያ በመለየት እንዲወዳደሩ ይጋብዛሉ።
በዚህ መሰረት በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ግዴታዎች ማሟላት አለባቸው።
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው፣ የዘመኑን ግብር ከፍሎ ንግድ ፈቃዱን ያሳደሰ እና እንዲሁም የግል ትራንስፖርት ድርጅት ከሆነ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው፤
- ከሚመለከተው ፈቃድ ሰጪ መንግስታዊ አካል የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድና የተጫራቾች ግዴታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 1000 በመክፈል ከዋልታ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 400,000 /አራት መቶ ሺህ ብር /ሲፒኦ/ CPO/ ማስያዝ አለባቸው ።
- የጨረታውን ሰነድ በኤንቨሎፕ በማሸግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይቻላል፤
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት በ10ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ ከቀኑ 8:30 ሰዓት የጨረታ ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዋልታ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ጽ/ቤት ይከፈታል። ነገር ግን 10ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታና ሁኔታ ጨረታው ታሽጎ ይከፈታል።
- ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
- ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር 0461151110/ 0916272305 / 0926854527 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻ፡-ምስራቅ ጉራጌ ዞን/ ቡታጅራ ከተማ
ዋልታ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ኃላ.የተወሰነ
Summary
Walta Farmers Cooperative Union (Butajira) seeks licensed dry cargo transporters to haul DAP and urea fertilizer from its Butajira central warehouse to woreda stations in East Gurage zone and Mareko special woreda for the 2019/20 season.
