የካፋ ሁለገብ ህብረት ሥራ ዩኒየን (ቦንጋ) የአፈር ማዳበሪያ ከቦንጋ መጋዘን ወደ ማራገፊያ ጣቢያዎች ለማጓጓዝ 200 ኩንታልና ከዚያ በላይ የመጫን አቅም ያላቸው የጭነት መኪናዎች ኪራይ ያወጣው የጨረታ ማስታወቂያ።
የደቡብ ምዕ/ኢት/ክልል የካፋ ሁለገብ ህብረት ስራ ዩኒየን ኃላ/የተወሰነ
የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ም/ኢት/ህ/ክ/መ/ በካፋ ዞን የካፋ ሁለ/ህ/ስራ ዩኒዩን በ2018 በጀት ዓመት ለዞኑ አርሶ አደሮች የሚያሰራጨውን ከቦንጋ ከተማ ካለው ዩኒዩኑ መጋዘን ወደ ተለያዩ ማራገፍያ ጣቢያዎች ለማጓጓዝ ከ200 እና በላይ ኩ/ል የመጫን አቅም ያለቸው የጭነት መኪና ኪራይ አገልግሎት የጨረታ መመሪያ
- ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ እና የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት የማይመለስ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው
- ተጫራቾች የባለቤትነት ማረጋገጫ /ሊብሬ/ መያዝ አለባቸው። የዘመኑ ኢንሹራንስ ስለመግባቱ ማረጋገጫ መያዝ አለበት ፤
- ተጫራቹ በቀጥተኛ ስራ መስክ ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ በመንግስት ግዥ ላይ በመሳተፍ በገቡት ውል መሰረት ስለማቅረባቸው የመልካም ስራ አፈጻጸም ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው።
- እያንዳንዱ ተጫራች ሞልቶ የሚያቀርበው ሰነድ የማይመለስ ብር 500 / አምስት መቶ ብር/ በኢ/ት/ን/ባንክ የዩኒዩኑ አካውንት ቁጥር 1000029085289 ላይ ገቢ በማድረግና ደረሰኝ በማቅረብ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት ዋጋ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ አድርጎ ራስን ማግለል አይችልም።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ የክፊያ ማዘዣ /CPO/200,000/ ሁለት መቶ ሺህ ብር/ ለካፋ ሁለ/ህብረት ስራ ዩኒዩን በማለት አሰርተው ከጨረታ ሰነድ ጋር በማዘጋጀት አያይዘ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ የጨረታ ማስከበሪያውን ከጨረታ ዶክመንት ጋር ያላስገባ ተጫራች ከጨረታ ይሰረዛል። ውጤቱ እንደታወቀ የጨረታ ማስከበሪያ ለተሸናፊ ተጫራቾች ወዲያውኑ ይመለሳል አሸናፊው ያቀረበው የጨረታ ማስከበሪያ የሚመለሰው የውል ማስከበሪያ የጠቅላላ ግዥ 10 ሰርሰንት ካስያዘ በኋላ ይሆናል።
- አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከሚመለከተው ክፍል ተገልፆለት ሁኑ በሚያዘው መሰረት ከሰባት የስራ ቀናት በኋላ ውል ከገባበት አንስቶ እስከ ነሀሴ 30/2019 ድረስ ውል የገባቸውን የመኪና ኪራይ አገልግሎት የጭነት ትዕዛዝ ከተሰጠበት ጊዜ አንስቶ በተፈለገ ጊዜ እና መጠን የመኪና ኪራይ አገልግሎት ባልተፈፀመበት የዋጋ ላይ 0.10 ከመቶ መቀጫ ይከፍላል።
- ይህ ውል ስምምነት እና የቀረበው ዋጋ እስከ ነሐሴ 30/2019 ዓ.ም ድረስ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል።
- እያንዳንዱ ተጫራች የሚወዳደርባቸው የመኪና ማንኛውም ወጪ የጥገና የነዳጅና ቅባት ፍጆታ እና የሹፌር ረዳት አበልና ደመወዝ ወጪ ከባለ መኪና ሆኖ የመኪና አገልግሎት ዝርዝር በነጠላ ዋጋ የማስቀመጥ ግዴታ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች በሚመለከተው የንግድ ስራ ዘርፍ ብቻ መወዳደር ያለበት ስሆን በሌላ ዘርፍ መወዳደር ተቀባይነት የለውም።
- እያንዳንዱ ተጫራች ዋጋ የተሞላበትን ኦርጅናልና አንድ ኮፒ በመለየት ፊርማና የድርጅቱን ማህተም በእያንዳንዱ ገጽ ላይ በማሳረፍ እና ፋይናንሻሉን በአንድ ፖስታ ቴክኒካሉን በአንድ ፖስታ በማሸግ ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታ ማሸጊያ ሰዓት ድረስ ዩንዩኑ ባለበት በንጋ ከተማ 01 ቀበሌ ባለ ቢሮ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ዋጋው በሚሞላበት ወቅት ስርዝ ድልዝ ወይም የማይነበብ ቁጥር ማስቀመጥ የለባቸውም።
- ሁሉም ዋጋ የሚሞላው የአንዱ ኩ/ል ነጠላ ዋጋ ነው።
- የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ህዳር 15/2019 ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ቅዳሜና እሁድ ጨምሮ አየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ ከ8:30 ላይ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቹ/በተገኙበት ይከፈታል፤ይሁን እንጂ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ያለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉልም።
- አሸናፍ ድርጅት ወይም ግለሰብ ማሸነፉ በድብዳቤ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ዋጋ እስከ በጀት አመቱ ማብቂያ ድረስ መቆየት ይኖርበታል።
- አሸናፍ ድርጅት ወይም ግለሰብ ያሸነፋበትን የመኪና ኪራይ አገልግሎት 200 እና በላይ ኩ/ል የመጫን አቅም ያላቸው ሆኖ የ2015 እና ከዚያ በላይ ሞዴል መኪና ያላቸው ባለንብረቶች የሚያቀርቡትን ለአ/አደር የሚከፋፈለውን የአፈር ማዳበሪያ በተጠቀሱ የማዳበሪያ ማራገፊያ ጣቢያዎች ዝርዝር ከዚህ ከተጫራቾች መመሪያ 01 ገፅ ተያይዞ ይቀርባል።
- የካፋ ሁ/ህ/ስራ ዩኒዬን እያንዳንዱ ተጫራች ከዚህ የዋጋ ማቅረቢያ ጋር በአባሪነት የተላከውን የግዥ የጨረታ ሰነድ መመሪያ አጠቃላይ ውልና ሰነድ በሚገባ በማንበብ ድርጅቱ አሸናፍ ቢሆን ውጤቱን ሙሉ በሙሉ ስለመቀበሉ የሚመለከተው የድርጅት ሀላፍ ፍርማና ማህተም በማሳረፍ ማረጋገጥ አለበት።
- ዩኒዩኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡- ማንኛውም በጨረታው ላይ መጠየቅ የፈለገ ተጫራች ተወዳዳሪ በስልክ ቁጥር 0913108240/0919137239 ላይ ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
በደ/ም/ኢት/ህ/ክ/መ/ በካፋ ዞን የካፋ ሁለ/ህ/ስራ ዩኒዩን
Summary
Kaffa Multipurpose Cooperative Union (Bonga, South West Ethiopia) rents cargo trucks of 200+ quintal capacity (2015 or newer) to carry fertilizer from its Bonga warehouse to distribution stations, priced per quintal. The contract runs to Nehase 30, 2019 EC.
