Tender Detail

Tender Details

  • Company የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሥራና ክህሎት ቢሮ
  • Address , Phone: 058-226-53-97
  • Website
  • Deadline03 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Priceብር 200 (የማይመለስ)
  • Bid Securityብር 350,000 (CPO ወይም የባንክ ዋስትና)
  • opening dateበዚሁ ቀን 4:30
  • Sector Furniture, Furnishing and Fixture

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሥራና ክህሎት ቢሮ የቢሮ ፈርኒቸሮች ግዥ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሥራና ክህሎት ቢሮ

Add to calendar Google Calendar Download .ics

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ስራና ክህሎት ቢሮ በ2019 በጀት ዓመት የቢሮ መገልገያ ፈርኒቸሮችን በሚወጣው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አካላት በጨረታ ሰነዱ መሠረት መወዳደር ይችላሉ።

በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ:-

1/ አግባብነት ያለው ህጋዊና በዘርፉ የተሰማራ ሆኖ በዘመኑ የታደሰ የንግድ የስራ ፈቃድና የታክስ ክሊራንስ ያለው::

2/ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የተቀበሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ::

3/ ግዥው ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ) በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴትታክስ /TAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

4/ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን የማይመለስ 200(ሁለትመቶ) ብር በመክፈል ቢሮ ቁጥር 001 መውሰድ ትችላላችሁ። ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላትና አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በፖስታ በማሸግ ከፖስታው ላይ በመጻፍ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል።

5/ ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በፖስታ በማሸግ ከጨረታ ማስከበሪያ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው።

6/ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን ወይም የዕቃውን ዋጋ ሲሞሉ በተቀመጠው እስፔክ መሰረት መሞላት ይኖርበታል።

7/ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለተከታታይ 10/አስር/ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል።

8/ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በባንክ በተመሰከረለት CPO /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ብር 350,000 (ሶስት መቶ ሃምሳ ሺህ)ማስያዝ ይኖርባችኋል።ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ጨረታ ሰነድ ላይ የተሞላን ዋጋ ማሻሻል ፣መለወጥ ወይም ጨረታውን ሰርዣለሁ የሚሉት ጥያቄዎች ተቀባይነት የላቸውም።

9/ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ10/አስር/ ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆይና በ11ኛው ቀን ማለትም 24/03/2019 ዓ/ም 4:00 ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የግዥ ገምጋሚ ኮሚቴው ቀድሞ ባዘጋጀው ቦታ ይከፈታል። የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜ፣ እሁድ ወይንም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል።ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም።

10/ ተጫራቾች ውደድሩ በሎት ድምር ስለሆነ የዕቃዎቹን ዋጋ ሙሉ በሙሉ መሙላት ይጠበቅባችኋል። ሙሉ በሙሉ ካልሞላችሁ ከጨረታ ውድድር ውጭ ይደረጋሉ።

12/ ቢሮው ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

13/ ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 058-226-53-97 መጠቀም ይችላሉ::

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሥራና ክህሎት ቢሮ

Summary
Amhara Regional State Labor and Skills Bureau invites bids to supply office furniture for the bureau by open bid. Bids are evaluated by lot total.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender