የደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ ለዞኑ ግብርና መምሪያ የፍራፍሬ ዘር ግዥ
የደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ
ሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ አገልግሎት ከሚሰጣቸው የዞን ሴክተር መ/ቤቶች ውስጥ አንዱ የሆነው የደ/ወሎ ዞን ግብርና መምሪያ የፍራፍሬ ዘር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም ከዚህ በታች በተዘረዘረው መስፈርት መሠረት መወዳደር ይችላሉ።
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ያላቸው፣
- የ2018 ዓ/ም የግብር ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ።
- የግዥ መጠኑ 500,000.00 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ የተመዘገቡ መሆናቸውን ሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፤
- ተጫራቾች ጥራት ያለው ዘር ማቅረብ እና በመ/ቤት ባለሙያ ማስፈተሽ አለባቸው።
- ማንኛውም ተጫራች በሰነዱ ላይ ሲሞሉ በእያንዳንዱ ዋጋ ላይ ቫትን ጨምሮ መሙላት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ዋጋ ብር 30,000/ሰላሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /c.p.o/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ደ/ወሎ ዞን ፋይናንስ ቡድን ገንዘብ ቤት መግዛት ይችላሉ።
- አሸናፊው አካል ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /C.P.O/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል።
- ጨረታ የሚወዳደረው በሎት /በጥቅል ዋጋ ድምር ነው።
- የአንዱ ዋጋ ወይም ጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ እንዲሁም የሞሉትን ዋጋ ጠቅላላ ድምር ካላስቀመጡ ጨረታ ውጭ ይሆናሉ።
- ማንኛውም ተጫራች ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለትበጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ በግዥ ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 610 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን መግዛትና በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው ተጫራቾች/ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት በግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 610 በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ይታሸጋል። በዚሁ ቀን ከረፋዱ 4:30 ሰዓት ይከፈታል። የመክፈቻው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ዕለት ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ታሽጎ 4:30 ይከፈታል።
- ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢ.ሮ ቁጥር 610 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033 111 81 18/19 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
- አሸናፊ ድርጅት የአሸነፉበትን ዘር በደ/ወሎ ወረዳዎች አምባሰል ወረዳ ሮቢትና ጢሳባሊማ ተሁለደሬ ወረዳ ጎበያ እና ጃሪ እንዲሁም ወረባቦ ወረዳ ቢስቲማ ንብረት ክፍል ድረስ በማድረስ ገቢ የሚያደርጉ ይሆናል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ እና ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ገንዘብ ቢሮ የደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ
Summary
South Wollo Zone Finance Department invites bids to supply fruit seeds for the zone agriculture department, delivered to stores in Ambassel, Tehuledere and Worebabo woredas.
