Tender Detail

Tender Details


በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የከምባታ ዞን ዶዮገና ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት የቢሮ መገልገያ ቋሚና አላቂ እቃዎች፣ የጽሕፈት መሳሪያ፣ ኮምፒውተር፣ ፕሪንተርና ኮፒ ማሽን ግዥ ያወጣው ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ።

የዶዮገና ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

Add to calendar Google Calendar Download .ics

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የከምባታ ዞን ዶዮገና ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛና በማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት በጀት የተለያዩ ቋሚ አላቂ የቢሮ መገልገያ የጽህፈት መሣሪያ ኮምፒውተር ፕሪንተር ኮፒ ማሽንና ሌሎች ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የመወዳደሪያ ሃሳብ በታሸገ ኢንቨሎፕ ውስጥ ሆኖ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15/ አስራ አምስት ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ ቀጣይ ቀን/አስራ ስድስተኛ/ ቀን ላይ የሚከፈት ይሆናል።ቀጣዩ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ላይ 4:00 ሰዓት ላይ ታሽጎ ወዲያውኑ ድርጅቱ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች ጠቀላላ ዋጋውን በቁጥርና በፊደል መጻፍ አለባቸው። በቁጥርና በፊደል በተገለጸው የዋጋ መጠን መካከል አለመጣጣም ካለ በፊደል የተገለጸው ተቀባይነት ይኖረዋል። በነጠላ ዋጋ እና በጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ካለ ነጠላ ዋጋው ተቀባይነት ይኖረዋል። ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሙሉ ዋጋውን 2% በCPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው።የጨረታ ማስከቢያ የዋስትና የሚቆይበት ጊዜ ጨረታው ከተከፈተበት ጊዜ አንስቶ ለ10/ አስር ተከታታይ ቀናት ሲሆን ዋስትናው ሊወረስ የሚችልባቸው ምክንያቶች እንደሚከተለው ይሆናል።ዋጋ ታክስ እንዳካተተ ተቆጥሮ ውድድሩ ይካሄዳል።በጨረታ ሰነድ ማሻሻያ መሰረት መ/ቤት የጨረታ መክፈቻ ጊዜውን እንደ አስፈላጊነቱ ለ7/ሰባት ቀናት ማራዘም ይችላል።

ተጫራቾች ሙሉ ግዥውና መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች(specification) ለሽያጭ በተዘጋጀው ሰነድ ተያይዟል።ተጫራቾች አሸናፊው አቅራቢ የሚለየው ለተጠየቁት ጠቅላላ ሥራዎች በሙሉ በድምሩ ዝቅተኛ ዋጋ አቅራቢው ይሆናል። በዚህ መስፈርት መሰረት ለሁሉም ሥራዎች ዝርዝር ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ከውድድ ውጪ ይሆናል።"ማንኛውም ተጫራች ከጨረታ መዝጊያ ቀንና ከዓት በፊትም በኋላም የዋጋ ማቅረቢያው ሰነድ/የመወዳደሪያ ሃሳብ ማስገባት የለበትም። ሂሳቡ ዋጋ የሚቀርበው በኢትዮጵያ ብር ይሆናል።

ተጫራቾች ሰነድ ይዘው ሲመጡ የትኛውን ሎት እንደሚወዳደሩ ለይተው መምጣት አለባቸው። የጨረታ ማወዳደሪያው በሚከተለው መሠረት ይሆናል። የቀረቡት ዕቃዎች ቴክኒካል መስፈርቶቹን ያሟሉ መሆናቸው የሚያረጋግጥ ሲሆን ውድድ 30/70 ነው።

  • የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው
  • TIN/የንግድ ምዝገበ ቁጥር ያለው
  • የቫት ተመዝጋቢ የሆነ
  • የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት
  • የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት
  • 2018/2025 ዓ/ም የታክስ ኪሊራንስ ማስረጃ 5/100
  • ጨረታው የቴክኒክ መስፈርቱን ካሟሉት አቅራቢዎች መካከል ዝቀተኛ ዋጋ ላቀረበው ተጫራች አሸናፊ ይደረጋል።
  • አሠሪው መ/ቤት ካቀረበው የዋጋ ጥናት ወደላይና ወደታች 15% በውድድሩ የሚታይ ይሆናል።
  • ተጫራች የሞላው ዋጋ ከታረመው ዋጋ ልዩነቱ ከ2% /ሁለት ፐርሰንት በላይ ከሆነ ከውድድሩ ውጪ ይሆናል።

የጨረታ ሰነድ ብር 300/ሦስት መቶ ብር/ እያንዳንዱ ሰነድ ለገቢዎች ጽ/ቤት ገቢ በማድረግ ከዶ/ከ/አስ/ግዥና ንብረት/አስ/ር ሥራ ሂደትመግዛት ይችላሉ።

ለበለጠ ስልክ ቁጥር 0916718624 /0911558711 /0913738073 ደውሎ መረጃ መውሰድ ይቻላል።

የዶዮገና ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት

Summary
Doyogena Town Administration Finance Office (Kembata zone, Central Ethiopia) buys office fixed assets and consumables, stationery, computers, printers, a copier and other items. Evaluation is 30/70 technical/financial; licensed, VAT-registered suppliers may bid.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender