አድማስ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን የአፈር ማዳበሪያ ማጓጓዝ አገልግሎት
አድማስ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን
የአፈር ማዳበሪያ ስለማጓጓዝ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ጨረታ ቁጥር አድገዩ/001/2019 ዓ.ም
አድማስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገ/ህ/ስራ ዩኒየን በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በጉራጌ ዞን ስር በሚገኙ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች አርሶ አደሮች በያዝነው 2019/20 የምርት ዘመን በወልቂጤ ከተማ ከሚገኘው ማእከላዊ መጋዘን ወደ ማራገፊያ ጣቢያዎች በበልግና በመኸር ዳፕ እና ኮሪያ የሰፈር ማዳበሪያ ለማጓጓዝ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከአድማስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገ/ህ/ስራ ዩኒየን በእያንዳንዱ ወረዳ የሚገኙ የማራገፊያ ጣቢያዎችን ዝርዝር መግለጫ በመውሰድ ለማጓጓዝ የሚፈለገውን የማድረሻ ዋጋ በጠጠርና በአስፓልት መንገድ በአማካኝ በኩንታል በአንድ ኪሎ ሜትር ተሰልቶ በእያንዳንዱ ጣቢያ በመለየት እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች :-
- በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍሎ ንግድ ፍቃዱን ያሳደሰ እና እንዲሁም የግል ትራንስፖርት ድርጅት ከሆነ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው
- ከሚመለከተው ፍቃድ ሰጪ መንግስታዊ አካል የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- የስራ ልምድ፡ ተጫራቾች የግብርና ግብአቶችን (ማዳበሪያ) ወይም ተመሳሳይ የጅምላ ጭነቶችን በማጓጓዝ ረገድ ቢያንስ 2 አመት ልምድ ያለው መሆን አለበት፣ ከቀድሞ ደንበኞቹም መልካም ስራ አፈጻጸም ያለው መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች ስራውን ከሌላ አካል በንኡስ ውል( Subcontaracting)ማስተላለፊ አይፈቀድለትም፤ በራሱ የሰራተኛ የተሸከርካሪ አቅም ማሟላት አለበት።
- የጨረታው ተሳታፊዎች ለአስተዳደር እንዲመች በአንድ ወረዳ ውስጥ በከፊል ዋጋ ማቅረብና መወዳደር አይችልም
- አጎራባች ወረዳዎችን ያሸነፉ የትራንስፖርት ደርጅቶች የተለያዩ በመሆናቸው ምክንያት በአጎራባች ወረዳዎች ስር በሚገኙ ማራገፊያ ጣቢያዎች መካከል ከፍተኛ የትራንስፖርት ዋጋ ልዩነት ከተፈጠረ ኪሎሜትርን መሰረት በማድረግ በአንድ ኪሎሜትር በተሰጠ ዝቅተኛ አማካኝ የአሸናፊ ዋጋ ይስተካከላል።
- በጨረታው ለመሳተፍ የማይመለስ ብር 1000 /አንድ ሺህ/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከአድማስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዩኒየኑ ፅ/ቤት ድረስ በመቅረብ ዘወትር በስራ ሰአት መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 450,000 /አራት መቶ ሀምሳ ሺ ብር/ ሲፒኦ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሰነድ በኢንቨሎፕ በማሸግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይችላል
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11:30 ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:30 የጨረታ ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አድማስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገ/ህ/ስራ ዩኒየን ጽ/ቤት ይከፈታል። ነገር ግን 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታና ሁኔታ ይከፈታል።
- ማንኛውም ተጫራች በግዴታ ውስጥ የተካተቱን ህጎች ማክበር የሚችል መሆን አለበት።
- ዩኒየኑ በትራንስፖርት ጨረታ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡
- ተጫራች ድርጅት ከዚህ በፊት በአድማስ ኃላ/የተ/የገ/ኅ/ስራ ዩኒየን የወጡ ጨረታዎችን ካሸነፈ በኋላ ግዴታውን በአግባቡ የተወጣ መሆን አለበት።
- ተጨማሪ መረጃ ቢያስፈልግ በስልክ ቁጥር:-0113301519/0936780943/0912775381 በመጠቀም ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
አድማስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገ/ህ/ስራ ዩኒየን/ጉራጌ ዞን ወልቂጤ/
Summary
Admas Farmers Cooperative Union (Wolkite, Gurage Zone) invites transporters to haul DAP and urea fertilizer from its central warehouse to unloading stations in woredas. Open bid.
