Tender Detail

Tender Details

  • Company ጊቤ ዲዴሳ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን (Gibe Dedesa Farmers Cooperative Union)
  • Address Nekemte, East Wollega Zone, Oromia, Phone: 0917035921
  • Website
  • Deadline11 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Price700(ሰባት መቶ ብር)
  • Bid Securityየጠቅላላ ዋጋ 5% CPO
  • opening dateታኅሣሥ 02/2019 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት
  • Sector Agriculture and Farming , Fertilizer , Warehousing and Store , Freight Transport

ጊቤ ዲዴሳ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን (ነቀምቴ) ለ2019/2020 ምርት ዘመን 571,473 ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ (DAP እና UREA) ለማጓጓዝ ደረቅ ጭነት አጓጓዦችን ለ2ኛ ዙር የጋበዘበት ግልጽ ጨረታ።

ጊቤ ዲዴሳ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን (Gibe Dedesa Farmers Cooperative Union)

Add to calendar Google Calendar Download .ics

ለ2ኛ ዙር የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በምስራቅ ወለጋ ዞን የሚገኘው ጊቤ ዲዴሳ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒዩን ለ2019/2020 ምርት ዘመን የሚውል የአፈር ማዳበሪያን ህጋዊ የደረቅ ጭነት አጓጓዦችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት የሚጓጓዘውን የአፈር ማዳበሪያ መጠን እና ዓይነት፡-

  1. DAP (ኤንፒኤስ)፡- 244,663 ኩንታል
  2. UREA (ዩሪያ)፡- 326,810 ኩንታል

ጠቅላላ ድምር 571,473 ኩንታል

ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር (10) ተከታታይ የሥራ ቀናት ሆኖ መስፈርቶቹ

  1. በዘርፉ ህጋዊ የስራ ፍቃድ እና የዘመኑን ግብር የ2019 የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  2. በሙሉ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበት የጠቅላላ ዋጋ 5% በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታው ከመከፈቱ በፊት አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የአፈር መደበርያ ለማጓጓዝ የ2019 ዓ.ም ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ እና የባለፈው ዓመት መልካም የሥራ አፈጻጸም ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡
  4. ከዩኒዩኑ ጋር ባለፉት ዓመታት በስራ አፈጻጸም መልካም ግንኙነት የሌላቸው ድርጅቶች ወይም ግለሰብ በጨረታው ውስጥ ዩንዮኑ ያለማሳተፍ መብት አለው፡፡
  5. ማንኛውም የምጫረትበትን የመኪና ብዛት 10 (አስር) እና ከዛ ባላይ ተሳብ መኪና ያለው ሆኖ ለዝሀም ከህጋዊ አካል ባለቤትነቱን የሚያረጋግጥ የመኪና ዝርዝር ማቅረብ አለበት፡፡
  6. ጨረታው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣ ቀን 18/03/2019 ጀምሮ እስከ 01/04/2019 ዓ.ም በምዕራብ ኦሮሚያ ነቀምቴ በሚገኘው ጊቤ ዲዴሳ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 3 ከቀኑ 11:00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 700.00 በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. የጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 02/04/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4:00 ሰዓት የጨረታ ሰነድ ኦሪጅናል እና ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ጊቤ ዲዴሳ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒዩን 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 3 በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ በማስገባት 02/04/2019 ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ በምዕራብ ኦሮሚያ ነቀምቴ በሚገኘው ጊቤ ዲዴሳ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒዩን ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች ዋጋ በሚያቀርቡበት ጊዜ የሚያጓጉዙበትን የአንድ ኩንታል እና ጠቅላላ በምወዳደሩበት መጋዘን ማነሻ እስከ መድረሻ ድረስ ከጨረታ ሰነድ ጋር ተያይዘው በቀረቡት ጣቢያዎች ላይ እንደቀርቡ ይገደዳሉ፡፡
  9. ማንኛውም ተጫራች በሚወዳደርበት ወረዳ ውስጥ በሁሉም የማራገፊያ ጣቢያዎች ላይ ዋጋ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
  10. በአንድ ማረገፊያ ጣቢያ ላይ ከሚቀርበው የአፈር ማዳበሪያ መጠን በታች (ከፋፍሎ) ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
  11. ለአንድ ኩንታል እና የጠቅላላ ዋጋ የተሰጠው የታሪፍ ዋጋ ልዩነት ካለው የአነስተኛ ታሪፍ ዋጋ ይወሰዳል፡፡
  12. ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
  13. አሸናፊው ድርጅት (ማህበር) ማሸነፉ በደብዳቤ ከተገለጸለት ዕለት ጀምሮ በ3 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጠቅላላ ዋጋ 5% የአፈጻጸም ዋስትና (Performance Bond) በማቅረብ ከዩኒዩኑ ጋር ውል መፈራረም አለበት፡፡
  14. አሸናፊው ድርጅት በሶስት ቀናት ውስጥ ቀርቦ የተጠቀሰው 5% የአፈጻጸም ዋስትና በማስያዝ ከዩኒዩኑ ጋር ካልተፈራረመ ዩኒዩኑ ለሚቀጥለው አሸናፊ ጨረታውን ይሰጣል፡፡
  15. የተያዘው የአፈጻጸም ዋስትና አጓጓዥ ለማጓጓዝ የወሰደውን የአፈር ማዳበሪያ አጓጉዞ እስኪ. ጨርስ ድረስ በዩኒዩኑ የሚያዝ ሲሆን በውሉ መሰረት ካላጓጓዘ ለዩኒዩኑ ገቢ ይሆናል፡፡
  16. ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ ከዋጋ ንረት በሚከሰቱ ነገሮች ዋጋ ለማስተካከል ዩኒዩኑ አይገደድም፡፡
  17. ዩኒዩኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በጨረታው አይገደድም ወይም በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- ጊቤ ዲዴሳ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን
ሞባይል 09 17035921 ወይም በስልክ ቁጥር 0576617841
ነቀምቴ

ጊቤ ዲዴሳ ኃላፊነቱ የተወሰነ የገበሬዎች ህብረት ስራ ዩኒየን

Summary
Gibe Dedesa Farmers Cooperative Union (Nekemte, East Wollega) re-tenders the transport of 571,473 quintals of DAP and UREA fertilizer for the 2019/2020 season. Bidders must own at least 10 trucks and hold a 2019 competence certificate.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender