የደቡቡ ኦሞ አርብቶአደር ሁለገብ ህብረት ሥራ ዩኒዬን በደቡብ ኦሞ ዞን በሚገኙ ወረዳዎች ላሉ አርሶ አደሮች በያዝነው 2019 ዓ ም በበልግ እና በመሄር የአፈር ማዳበሪያ (NBSB እና UREA) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል።
የደቡብ ኦሞ አርብቶ አደር ሁለገብ ህብረት ስራ ዩኒዬን
የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ጨረታ ማስታወቂያ
የደቡቡ ኦሞ አርብቶአደር ሁለገብ ህብረት ሥራ ዩኒዬን በደቡብ ኦሞ ዞን በሚገኙ ወረዳዎች ላሉ አርሶ አደሮች በያዝነው 2019 ዓ ም በበልግ እና በመሄር የአፈር ማዳበሪያ (NBSB እና UREA) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከድርጅቱ የማራገፊያ ጣቢያዎችን ዝርዝር መግለጫ በመውሰድ ለማጓጓዝ የሚፈለገውን የማድረሻ ዋጋ በጠጠርና በአስፋልት መንገድ በአማካይ በኩንታል በአንድ ኪሎ ሜትር ተሰልቶ በእያንዳንዱ ጣቢያ በመለየት እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
በዚሁ መሰረት ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች
- በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ያለው ፤የዘመኑን ግብር የከፈለና ንግድ ፍቃዱን ያሳደሰ እንዲሁም የግል ትራንስፖርት ድርጅት ከሆነ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው ::
- ከሚመለከተው ፈቃድ ሰጪ መንግስታዊ አካል የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ የስራ ዘርፍ ተሰማርቶ ስራውን በሚገባ ስለመወጣቱ የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችል ።
- የጨረታው ተሳታፊዎች ለአስተዳደር እንዲያመች በአንድ ወረዳ ውስጥ በከፍል ዋጋ ማቅረብና መወዳደር አይችሉም
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት የጨረታ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ ብር 300 000/ ሶስት መቶ ሺህ / ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- በጨረታ አሸናፊ የሚሆን ማንኛውም ድርጅት ውል ከመፈፀሙ በፊት ያሸነፈበትን ጭነት ማጓጓዣ ዋጋ 10 % ቅድሚያ ያስዛል።
- ተጫራቾች የተሽከርካሪዎች ዝርዝር ቢያንስ 2000 /ሁለት ሺህ /ኩንታል በአንድ ጊዜ ለማንሳት የሚችሉ መኪኖችን የሰሌዳ ቁጥር ፤የመኪና አይነትና የመጫን አቅም የሚያስረዳ ፈቃድ ከሰጠው መንግስታዊ አካል የተሰጠው ወቅታዊ መረጃ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድና የተጫራቾች ግዴታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በደቡብ ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 800 /ስምንት መቶ/ በመክፈል ከደቡብ ኦሞ አርብቶ አደር ሁለገብ ህብረት ስራ ዩኒዬን ዋና ጽ/ቤት ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታውን ሰነዶች በኢንቨሎፕ በማሸግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/ አስር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይችላል።
- ይህ የጨረታ ማስታውቂያ በወጣ በ10ኛው ቀን ከቀኑ 11:00 ሰዓት ታሽጎ በ 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ተሳታፊዎች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዩኒዬኑ ዋና ጽ/ቤት ይከፈታል ነገር ግን 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ከላይ በተለገጸው ቦታና ሁኔታ ይከፈታል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ በምቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ: ቀይ አፈር ከተማ ከመስጊዱ ጀርባ
ስልክ ቁጥር-0916061351/0916406754
የደቡብ ኦሞ አርብቶ አደር ሁለገብ ህብረት ስራ ዩኒዬን
Summary
South Omo Pastoralist Multipurpose Cooperative Union invites transporters to bid for hauling NBSB and urea fertilizer to unloading stations in South Omo Zone woredas, priced per quintal per km.
