Tender Detail

Tender Details

  • Company ዳሞታ የወላይታ ገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን
  • Address ወላይታ ሶዶ መናኸሪያ ፊት ለፊት ወደ ኦቶና በሚወስደው አስፋልት ላይ ሙሐባና ቻይና ጋራዥ ጎን ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 046 551 0642
  • Website
  • Deadline14 Dec 2026, 5:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Price1000(አንድ ሺህ ብር)
  • Bid Securityብር 500,000 በባንክ የተረጋገጠ CPO
  • opening dateበ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት (የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን)
  • Sector Warehousing and Store , Freight Transport

ዳሞታ የወላይታ ገበሬዎች ሁለገብ ህብረት ሥራ ዩኒየን (ወላይታ ሶዶ) የ2019 ምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ ዳፕና ዩሪያ ከማዕከላዊ መጋዘኖች ወደ ወላይታ ዞን ማራገፊያ ጣቢያዎች ለማጓጓዝ ያወጣው የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ጨረታ (ቁጥር 009/2019)።

ዳሞታ የወላይታ ገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን

Add to calendar Google Calendar Download .ics

የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ጨረታ ቁጥር 009/2019

ዳሞታ የወላይታ ገ/ሁ/ሥራ ዩኒየን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በወላይታ ዞን ለሚገኙ አርሶ አደሮች በያዝነው ምርት ዘመን 2019 ከወላይታ ሶዶ ከተማ እና ከቡራ ኮዶ ከሚገኙ ማዕከላዊ መጋዘኖች ለማራገፊያ ጣቢያዎች ለበልግ፣መኸርና መስኖ የአፈር ማዳበሪያ/ዳፕ/ እና ዩሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾች ከድርጅቱ የማራገፊያ ጣቢያዎችን ዝርዝር መግለጫ መሠረት ለማጓጓዝ የሚፈልገውን የማድረሻ ዋጋ በጠጠርና በአስፋልት መንገድ በአማካይ በኩንታል በአንድ ኪሎ ሜትር ተሰልቶ በእያንዳንዱ ጣቢያ በመለየት እንድወዳደሩ ይጋብዛል።

በዚሁ መሠረት

  1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው የዘመኑ ግብር ከፍሎ የንግድ ፍቃዱን ያሳደሰ እንድሁም የግል ትራንስፖርት ድርጅት ከሆነ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው/ ያላት/፤
  2. ከሚመለከተው ፍቃድ ሰጪ መንግስታዊ አካል የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ፤
  3. ከዚህ ቀድም በተመሳሳይ የሥራ ዘርፍ ተሰማርቶ ስራውን በሚገባ ሰለመወጣቱ የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችል፤
  4. የጨረታው ተሳታፊዎች ለአስተዳደር እንዲያመች በአንድ ወረዳ ወይም ማራገፊያ ጣቢያ ውስጥ በከፊል ዋጋ ማቅረብና መወዳደር አይችሉም፤
  5. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ስፒኦ /CPO/ ብር 500,000 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  6. በጨረታ አሸናፊ የሚሆን ማንኛውም ድርጅት ውል ከመፈጸሙ በፊት ያሸነፈበትን ጭነት ማጓጓዣ ዋጋ 10 ፐርሰንት ለውል ማስከበሪያ በቅድሚያ ያስይዛል፤
  7. ተጫራቾች የተሽከርካሪዎችን ዝርዝር ቢያንስ 2,400 /ሁለት ሺህ አራት መቶ ኩንታል /በአንድ ጊዜ ለማንሳት የሚችሉ መኪኖችን የሠሌዳ ቁጥር የመኪና ዓይነት እና የመጫን አቅም የሚያስረዳ ፈቃድ ከሰጠው መንግስታዊ አካል የተሰጠ ወቅታዊ መረጃ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
  8. የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድና የተጫራቾች ግዴታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር1000 /አንድ ሺህ ብር/ በመክፈል ከዳሞታ የወላይታ ገ/ሁ/ሥ/ ዩኒየን ዋና ጽ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላል፤
  9. የጨረታውን ሰነድ በኢንቨሎፕ በማሸግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 /ሃያ አንድ /ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይችላል፤
  10. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት በ21ኛው ቀን ከቀኑ 11:00 ሰዓት ታሽጎ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት የጨረታ ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዩኒየኑ ዋና ጽ/ቤት ይከፈታል። ነገር ግን 22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታና ሁኔታ ይከፈታል።
  11. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. የጨረታ አሸናፍ የሆነ ድርጅት በመስፈርቱ መሠረት ማሸነፉ ስረጋገጥ በዩኒዬን ማስታወቂያ ቦርድ የሚገለፅ ይሆናል።

አድራሻ ወላይታ ሶዶ መናሐሪያ ፊት ለፊት ወደ አቶና በሚወስደው አስፋልት ላይ ሙሐባና ቻይና ጋራጅ ጎን ይገኛል።

ስልክ ቁጥር 0465510642//0975064075/0913832626/0910432549
ፋክስ 0465522955

ዳሞታ የወላይታ ገበሬዎች ሁለገብ ህብረት ሥራ ዩኒየን ወ/ሶዶ

Summary
Damota Wolaita Farmers Multipurpose Cooperative Union (Wolaita Sodo) seeks licensed dry cargo transporters to haul DAP and urea fertilizer from its central warehouses to unloading stations across Wolaita zone. Trucks must lift 2,400 quintals at once.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender