የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የተለያዩ የጨርቅ ቦርሳ፣ ዣንጥላ እና ሰደሪያ ዕቃዎች ግዥ ያወጣው ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ።
SIDAMA NATIONAL REGIONAL STATE HEALTH BUREAU (የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ)
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ የተለያዩ የጨርቅ ቦርሳ፣ዣንጥላ እና ሰደሪያ ዕቃዎች በጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡
በዚሁ መሠረት፤
- የንግድ ፍቃዳቸው የምዝገባ ሠርተፍኬታቸውን ለ2019 ዓ.ም ያሳደሱ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ ጨረታውን በክልል ሲዳማ ጤና ቢሮ በማቅረብ ለግዥ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከቢሮ ቁጥር 27 መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች አጠቃላይ ዋጋ CPO 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ የጨረታ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችል፣ ሆኖም በሂሳብ ስሌት ምርመራ የተገኘው የጨረታ ዋስትና ከቀረበው ዋጋ በታች ሆኖ ከተገኘ ከጨረታ ውጪ ያስደርጋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዳቸውን ቴክኒካልና ፋይናንሻል ለእያንዳንቸው አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፣በመሆኑም ከዚህ በላይ ከተገለጸው ውጪ የሚያቀርቡ ከውድድር ወጪ ያስደርጋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ በተጠየቀው መሠረት ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፣
- ጨረታው በ11ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ ከ4-6:00 ሰዓት ድረስ የግ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ግዥ ክፍል በተዘጋጀው ጨረታ ሣጥን በማስገባት በተጠቀሰው ሰዓቱ ይታሸጋል፤ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8:30 ሰዓት ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት ይከፈታል 11ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0462125847 ይጠይቁን
ሲ/ብ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ
Summary
Sidama Regional Health Bureau buys various cloth bags, umbrellas and vests by open tender. Bidders with a licence renewed for 2019 EC, TIN and VAT registration may bid.
