Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Press Agency (የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)
  • Address አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-1-56-98-69
  • Websitehttps://press.et/
  • Deadline07 Dec 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Price100(አንድ መቶ ብር)
  • Bid Securityብር 50,000.00 CPO ወይም ቢድ ቦንድ
  • opening dateበዕለቱ ከረፋዱ 4:30 ሰዓት
  • Sector Consultancy Service , Engineering Service

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት የግንባታ አማካሪ አገልግሎት ግዥ ለመፈጸም ያወጣው ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር ኢፕድ 015/2019)።

Ethiopian Press Agency (የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)

Add to calendar Google Calendar Download .ics

ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር፡-ኢፕድ 015/2019

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2019 በጀት ዓመት የግንባታ አማካሪ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።በዚህም መሰረት፡- ስለሆነም፡-ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በውድድሩ መሳተፍ ይችላሉ።

  1. በሥራ ዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት ፣በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ታክስ ክሊራንስና በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸዉ።
  2. ዕጩ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ግዥዉን አስመልክቶ የተዘጋጀዉን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምሪያ ግዥ ቡድን በአካል በመምጣት ይህ የጨረታ ማስታወቂያዉ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት በመውሰድ የሚወዳደሩበትን ዝርዝር ዋጋ ከቫት ጋር በመሙላት፣ የጨረታ ሰነዱን በ4 በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦሪጅናሉንና ኮፒዎቻቸዉን ለየብቻ በማቅረብ ጉዳዩን አስመልክቶ በተዘጋጀዉ በአቅርቦት መምሪያ ግዥ ቡድን በሚገኘዉ የጨረታ ሳጥን ዉስጥ ማስገባት አለባቸዉ።
  3. ዕጩ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበርያ የሚዉል ብር 50,000.00(ሀምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ/ቢ.ድቦንድ ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ከአደረጃቸዉ አካል የሚሰጥ ዋስትና ደብዳቤ ማስያዝ አለባቸዉ።
  4. ጨረታዉ ዕጩ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛዉ የሥራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ በአቅርቦት መምሪያ ከረፋዱ 4:00 ሠዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ 4:30 ሰዓት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምሪያ ግዥ ቡድን 1ኛ ፎቅ ይከፈታል። ሆኖም ግን የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
  5. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

ስልክ ቁጥር 011 1 56 98 69
ኢ.ሜይል procurement@press.et
አድራሻ ፡አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊትለፊት

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

Summary
Ethiopian Press Agency invites licensed consulting firms to bid for construction consultancy (supervision) services for its 2019 EC budget year. Bidders need a renewed licence, TIN, VAT, tax clearance and public procurement supplier registration.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender