Tender Detail

Tender Details

  • Company የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማህበር
  • Address አዲስ አበባ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 9 የቤት ቁጥር 521፣ መስቀል አደባባይ ኤግዚቢሽን ማእከል ጀርባ, Phone: 0115576162
  • Website
  • Deadline28 Nov 2026, 4:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Price500(አምስት መቶ ብር)
  • Bid Securityብር 5,000.00 CPO
  • opening dateበማግስቱ የስራ ቀን ከረፋዱ 4:00 ሰዓት
  • Sector Consultancy Service

የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማህበር በኮልፌ ቀራኒዮ ወረዳ 2 በሚገኘው ይዞታው ላይ ለሚገነባው የንግድና የቢሮ ሕንፃ የገበያ፣ ቴክኒክ፣ ፋይናንስና ኢኮኖሚ አዋጭነት ጥናት ለማሰራት አማካሪ ድርጅቶችን የጋበዘበት ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ።

የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማህበር

Add to calendar Google Calendar Download .ics

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የንግድና የቢሮ ሕንፃ ገበያና አዋጭነት ጥናት አገልግሎት ግዥ የድርጅቱ ስም፡- የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማህበር ድርጅታችን ለትርፍ ያልተቋቋመ ተቋም ቢሆንም፣ የድርጅቱን የፋይናንስ ዘላቂነት ለማጠናከርና ተቋማዊ ተልዕኮውን በቀጣይነት ለማስፈጸም የሚያስችል የገቢ ምንጭ ለማልማት ቀደ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ ከተማ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 በሚገኘው የድርጅቱ ይዞታ ላይ የንግድና የቢሮ ሕንፃ ለመገንባት አቅዷል።

ስለሆነም የታቀደው ፕሮጀክት የገበያ ፍላጎት፣ የቴክኒክ፣ የፋይናንስና የኢኮኖሚ አዋጭነት ለመገምገም፣ ተገቢውን የልማት አማራጭ ለመለየትና ለትግበራ የሚያግዝ ዝርዝር ጥናት ለማሰራት በዘርፉ ብቃትና ልምድ ያላቸውን የአማካሪ ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ ለማወዳደር ይፈልጋል።

1. የጥናቱ ዓላማ፡-

የጥናቱ ዋና ዓላማ በድርጅቱ ይዞታ ላይ የሚገነባው የንግድና የቢሮ ሕንፃ የገበያ፣ የቴክኒክና የፋይናንስ አዋጭነት መገምገም እና ለድርጅቱ ዘላቂ የገቢ ምንጭ የሚሆን ተገቢ የልማት አማራጭ ማቅረብ ነው።

2. የጥናቱ የሥራ ወሰን (Scope of Work)

ተመራጩ አማካሪ ድርጅት ቢያንስ የሚከተሉትን ሥራዎች ማከናወን ይጠበቅበታል።

  1. የገበያ ጥናት (Market Study) በኮልፌ ቀራኒዮ ወረዳ 2 የሚገኘው በአካባቢው የንግድና የቢሮ ቦታ ፍላጎት፣ የኪራይ ዋጋ፣ የተፎካካሪ ሕንፃዎችና የደንበኞች ፍላጎት መተንተን፣
  2. የቴክኒክ ጥናት (Technical Feasibility) የመሬቱን ሁኔታ፣ የሕንፃ አቀማመጥ፣ የወለል ብዛት፣ የግንባታ ስፋትና የአጠቃቀም አማራጮችን መገምገም፣
  3. የፋይናንስ አዋጭነት (Financial Feasibility) የግንባታ ወጪ፣ የሥራ ማስኬጃ ወጪ፣ የኪራይ ገቢና የተጣራ የገንዘብ ፍሰት ትንበያ ማዘጋጀት፣
  4. የኢኮኖሚ ትንተና፡- ፕሮጀክቱ ለድርጅቱ የሚያስገኘውን የገቢ እድልና የፋይናንስ ዘላቂነት መገምገም፣
  5. የአደጋ ትንተና፡- የግንባታ ወጪ ጭማሪ፣ የገበያ ለውጥ፣ የኪራይ ፍላጎትና የባዶ ቦታ መጠን ተፅዕኖ መተንተን፣
  6. የአማራጮች ንጽጽር፡- የተለያዩ የሕንፃ ዲዛይንና የአጠቃቀም አማራጮችን በወጪ፣ በገቢና በትርፋማነት ማነፃፀር፣
  7. የትግበራ ዕቅድ፡- የፕሮጀክቱን የግንባታ ደረጃዎች የጊዜ ሰሌዳ፣ የፋይናንስ ስፍላጎትና የትግበራ ስትራቴጂ ማቅረብ።

3. የሚቀርቡ የጥናት ውጤቶች (Deliverables)

  1. የገበያ ጥናት ሪፖርት፣
  2. የቴክኒክ አዋጭነት ጥናት፣
  3. የግንባታ ወጪ ግምት፣
  4. የፋይናንስ ሞዴልና የገቢ ትንበያ፣
  5. የNPV፣ IRR፣ Payback Period እና Sensitivity Analysis ውጤቶች፣
  6. የተመራጭ የፕሮጀክት አማራጭ ምክረ ሀሳብ
  7. የመጨረሻ ዝርዝር የአዋጭነት ጥናት ሪፖርት።

4. የተጫራቾች ብቃትና መስፈርቶች፡-

  1. በሕጋዊ መንገድ የተቋቋመና የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያለው መሆን፣
  2. በገበያና አዋጭነት ጥናት የተለየ ልምድ ያለው መሆን፣
  3. በፋይናንስ፣ በኢኮኖሚክስ፣ በአርኪቴክቸርና በሲቪል ኢንጂነሪንግ ዘርፎች ብቃት ያላቸው ባለሙያዎችን ማቅረብ፣
  4. ተመሳሳይ ፕሮጀክቶችን የሠሩበትን ማስረጃ ማቅረብ።

5. የሚቀርቡ የጨረታ ሰነዶች

  1. የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣
  2. TIN እና የግብር ክሊራንስ፣
  3. የድርጅቱ መገለጫና የሥራ ልምድ ማስረጃ፣
  4. የቴክኒክ ሀሳብ (Technical Proposal)፣
  5. የፋይናንስ ሀሳብ (Financial Proposal)፣
  6. የባለሙያዎች CV እና የትምህርት ማስረጃዎች፣
  7. የቀድሞ ተመሳሳይ ሥራዎች ማስረጃ።

6. የጨረታ ማቅረቢያና መክፈቻ

  • ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የምታሟሉና ስራውን የምትሰሩበት የአገልግሎት ዋጋ በመሟላት መረጃዎችሁን የቴክኒክና የፋይናንስ ሰነዶች በተለያዩ በስማቹ በታሸገ ኢንቨሎፕ አያይዛችሁ በጨረታ እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን።
  • የጨረታ ማስከበሪያ ብር 5000.00 ብር /አምስት ሺ ብር/ በሲፒኦ በማስያዝ የጨረታ ሰነድ በብር 500.00/ብር አምስት መቶ/ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
  • ጨረታው የሚቆየው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሰባት የስራ ቀናት ሲሆን የሚከፈተው በማግስቱ የስራ ቀን ከረፋዱ 4:00 ሰዓት ተጫራቾች ( ወኪል) በተገኙበት ይከፈታል።
  • ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የሰነድ ማቅረቢያ ቦታ፡- ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 9 የቤት ቁጥር 521 መስቀል አደባባይ ኢግዚቢሽን ማእከል ጀርባ
ስልክ ቁጥር፡- 0115576162 / 0911440933 / 0985821799/ 0911346192
አዲስ አበባ

የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማህበር

Summary
Addis Ababa City Women's Association seeks consulting firms for a market, technical, financial and economic feasibility study of a planned commercial and office building on its plot in Kolfe Keranio Woreda 2, including NPV/IRR analysis and an implementation plan.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender