Tender Detail

Tender Details

  • Company የጋሞ ገበሬዎች አትክልትና ፍራፍሬ ህብረት ሥራ ዩኒየን
  • Address አርባ ምንጭ፣ ሲቀላ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጎን (gamogofaunion@gmail.com), Phone: 0468811445
  • Website
  • Deadline30 Nov 2026, 5:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document Price600(ስድስት መቶ ብር)
  • Bid Securityብር 300,000.00 በባንክ የተረጋገጠ CPO
  • opening dateበ8ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት (የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን)
  • Sector Warehousing and Store , Freight Transport

የጋሞ ገበሬዎች አትክልትና ፍራፍሬ ህብረት ሥራ ዩኒየን (አርባ ምንጭ) የ2019 ዓ.ም ምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ DAP/NPSB እና ዩሪያ ከአርባ ምንጭ ማዕከላዊ መጋዘኖች ወደ ጋሞ ዞን ወረዳዎች ለማጓጓዝ ያወጣው የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ጨረታ (ቁጥር 008/2019)።

የጋሞ ገበሬዎች አትክልትና ፍራፍሬ ህብረት ሥራ ዩኒየን

Add to calendar Google Calendar Download .ics

የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ጨረታ

ቁጥር 008/2019

የጋሞ ገበሬዎች አትክልትና ፍራፍሬ ህብረት ሥራ ዩኒየን በደቡብ ኢትዮጵያ ክ/መንግስት በጋሞ ዞን ፤አርባ ምንጭ ከተማ አስተዳደር እና በአሌ ዞን ባሉት ወረዳዎች ለአርሶ አደሮች በያዝናቸው ምርት ዘመን 2019 ዓ.ም አ/ምንጭ፤ ከተማ ከሚገኙ ማዕከላዊ መጋዘኖች ለጣቢዎች ለበጋ መስኖ፣ለበልግና መኸር የአፈር ማዳበሪያ DAP/NPSB /ምጥን/ እና ዩሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት፡-

  1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው. የዘመኑ ግብር ከፍሎ የንግድ ፍቃዱን ያሳደሰ፣ እንዲሁም የግል ትራንስፖርት ድርጅት ከሆነ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው/ ያላት እና ከተደራጁበት አካባቢ ከገቢዎች የተሠጠ ከልራንስ ያለው/ያላት መሆን አለበት።
  2. ከሚመለከተው ፍቃድ ሰጪ መንግስታዊ አካል የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  3. ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ የሥራ ዘርፍ ተሰማርቶ ስራን በሚገባ ስለመወጣቱ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ሁለትና ከዚህ በላይ ማቅረብ የሚችል፤
  4. የጨረታው ተሳታፊዎች ለአስተዳደር እንዲያመች በአንድ ወረዳ ወይም ማራገፊያ ጣቢያ ውስጥ በከፊል ዋጋ ማቅረብና መወዳደር አይችሉም፤
  5. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  6. በጨረታ አሸናፊ የሚሆን ማንኛውም ድርጅት ውል ከመፈፀሙ በፊት ያሸነፈበትን ጭነት ማጓጓዣ ዋጋ ፐርሰንት ለውል ማስከበሪያ በቅድሚያ ያስይዛል፤
  7. ተጫራቾች የተሽከርካሪዎች ዝርዝር ቢያስ 2,400 ኩ/ል (ሁለት ሺህ አራት መቶ ኩንታል) በአንድ ጊዜ ለማንሳት የሚችል መኪኖችን የሠሌዳ ቁጥር፣ የመኪና ዓይነት እና የመጫን አቅም የሚያስረዳ ፈቃድ ከሰጠው መንግስታዊ አካል የተሰጠ ወቅታዊ መረጃ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
  8. የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድና የተጫራቾች ግዴታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 600.00 (ስድስት መቶ ብር) በመክፈል ከጋሞ ገበሬዎች አትክልትና ፍራፍሬ ግብይት ህብረት ሥራ ዩኒየን ዋና ጽ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላል፤
  9. የጨረታውን ሰነድ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7(ሰባት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማቅረብ ይችላል።
  10. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት በ7 ኛው ቀን ከቀኑ 11:00 ሰዓት ታሽጎ በ8 ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት የጨረታ ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዩኒየኑ ዋና ጽ/ቤት ይከፈታል። ነገር ግን 8 ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጣዩ የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሁኔታ ይከፈታል።
  11. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- ሲቀላ፤ አ/ምንጭ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጎን
ስልክ፡- 046- 881- 1445/ 0930003217/0967000718
ፋክስ፡- 046 - 881 - 3817
E.mail:- gamogofaunion@gmail.com

የጋሞ ገበሬዎች አትክልትና ፍራፍሬ ህብረት ሥራ ዩኒየን

Summary
Gamo Farmers Fruit and Vegetable Cooperative Union (Arba Minch) seeks licensed dry cargo transporters to haul DAP/NPSB and urea fertilizer from Arba Minch central warehouses to woreda stations in Gamo and Ale zones. Trucks must lift 2,400 quintals at once.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender