ካዮ ኃ/የተ ሁለገብ አትክልትና ፍራፍሬ ግ/ህ/ሥ/ዩኒየን (ዲላ) የ2019 ዓ.ም ምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ ዳፕና ዩሪያ ከዲላ መጋዘን ወደ ጌዴኦ ዞን ወረዳዎች ማራገፊያ ጣቢያዎች ለማጓጓዝ ያወጣው የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ጨረታ (ቁጥር 003/19)።
ካዮ አትክልትና ፍራፍሬ ግ/ህ/ሥ/ዩ/ኃ/የተ
የጨረታ ማስታወቂያ
የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ጨረታ ቁጥር 003/19
ካዮ ኃ/የተ ሁለገብ አትክልትና ፍራፍሬ ግ/ህ/ሥ/ዩኒየን በደ/ኢ/ክ/መንግስት በጌዴኦ ዞን ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደር አ/አደሮች በያዝነዉ ምርት ዘመን 2019 ዓ.ም ከዲላ ከተማ ከሚገኘ መጋዘን ወደ ማራገፊያ ጣቢያዎች ለበልግ፣ መኸርና መስኖ የአፈር ማዳበሪያ ዳፕ እና ዩሪያ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች ከድርጅቱ የማራገፊያ ጣቢያዎች ዝርዝር መግለጫ መሠረት ለማጓጓዝ የሚፈልገውን የመዳረሻ ዋጋ በጠጠር እና በአስፋልት መንገድ በአማካይ በኩንታል በአንድ ኪሎ ሜትር ተሰልቶ በእያንዳንዱ ጣቢያ በመለየት እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
በዚሁ መሠረት፡-
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው የዘመኑ ግብር ከፍሎ የንግድ ፍቃዱን ያሳደሰ እንዲሁም የግል ትራንስፖርት ድርጅት ከሆነ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው /ያላት/።
- ከሚመለከተው ፍቃድ ሰጭ መንግስታዊ አካል የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
- ከዚህ ቀደም በተመሳሳይ የሥራ ዘርፍ ተሰማርቶ ስራውን በሚገባ ስለመወጣቱ የመልካም ስራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችል።
- የጨረታው ተሳታፊዎች ለአስተዳደር እንዲያመች በአንድ ወረዳ ወይም ማራገፊያ ጣቢያ ወስጥ በከፊል ዋጋ ማቅረብ እና መወዳደር አይችሉም።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብር 500,000 /አምስት መቶ ሺህ ብር/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- በጨረታ አሸናፊ የሚሆን ማንኛዉም ተጫራች ዉል ከመፈጸሙ በፊት ያሸነፈበትን የጭነት ማጓጓዣ ዋጋ 10 ፐርሰንት ለዉል ማስከበሪያ በቅድሚያ ያስይዛል።
- ተጫራቾች የተሽከርካሪዎችን ዝርዝር ቢያንስ 100 (አንድ መቶ) ኩንታል በአንድ ጊዜ ማንሳት የሚችሉ መኪኖችን የሰሌዳ ቁጥር፣ የመኪና አይነት እና የመጫን አቅም የሚያስረዳ ፈቃድ ከሰጠዉ መንግስታዊ አካል የተሰጠ ወቅታዊ መረጃ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ እና የተጫራቾች ግዴታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 2000 /ሁለት ሺህ ብር/ በመክፈል ከካዮ አ/ፍ ግ/ህ/ሥ/ዩ/ኃ/የተ ጽ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይቻላል።
- የጨረታውን ሰነድ በኤንቨሎፕ በማሸግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 /ሃያ አንድ/ ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ማቅረብ ይችላል።
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ታትሞ ከወጣበት በ21ኛው ቀን ከቀኑ 11:00 ሰዓት ታሽጎ በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:30 ሰዓት የጨረታ ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዩኒየኑ ዋና ጽ/ቤት ይከፈታል። ነገር ግን 22ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ቀጣዩ የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታና ሁኔታ ይከፈታል።
- ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
አድራሻ፡- በጌዴኦ ዞን ሕብረት ስራ ልማት ጽ/ቤት ግቢ ዉስጥ ይገኛል።
ስልክ ቁጥር 0916189564
ካዮ ኃ/የተ ሁለገብ አትክልትና ፍራፍሬ ግ/ህ/ሥ/ዩኒየን ዲላ
Summary
Kayo Multipurpose Fruit and Vegetable Farmers Cooperative Union (Dilla) seeks licensed dry cargo transporters to haul DAP and urea fertilizer from its Dilla warehouse to woreda unloading stations in Gedeo zone. Trucks must carry at least 100 quintals each.
