Tender Detail

Tender Details

  • Company Oromia Pipe Factory PLC (ኦሮሚያ ፓይፕ ፋብሪካ የተ/የግ/ማህበር)
  • Address ቃሊቲ አሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ቅጥር ግቢ ጀርባ፡ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-4-395-911
  • Website
  • Deadline04 Dec 2026, 2:00 PM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityብር 2,000.00 CPO (Oromia pipe Factory PLC)
  • opening dateህዳር 25 ቀን 2019 ዓ.ም. ወዲያውኑ በ8:00 ሰዓት
  • Sector Labour Outsourcing Services

የኦሮሚያ ፓይፕ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከውጭና ከሀገር ውስጥ ለሚያስገባቸው የፋብሪካ ጥሬ ዕቃዎች (HDPE፣ ሬዚን፣ ካልሲየም ካርቦኔት፣ ስታብላይዘር፣ ካርበን ብላክ) የጫኝና አውራጅ አገልግሎት በኮንትራት ለማሰራት በድጋሚ ያወጣው ግልጽ ጨረታ (ቁጥር OPF/2026/19/003)።

Oromia Pipe Factory PLC (ኦሮሚያ ፓይፕ ፋብሪካ የተ/የግ/ማህበር)

Add to calendar Google Calendar Download .ics

በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር OPF/2026/19/003

ድርጅታችን የኦሮሚያ ፓይፕ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግል ማህበር ከውጭ ሀገር እና ከሀገር ውስጥ ለሚያስገባቸው የፋብሪካ ጥሬ ዕቃዎች ቀጥለው በተዘረዘረው መሠረት ህጋዊ መስፈርቶችን የሚያሟሉ በዚህ ስራ ላይ የተሰማሩትን አውራጆችን አወዳድረው በኮንትራት ማሰራት ይፈልጋል። ስለሆነም መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ።

ተ.ቁየጥሬ ዕቃው ዓይነትመለኪያብዛትበ20ft ኮንቴይነርበ40ft ኮንቴይነርያለኮንቴይነር ከጂቡቲ እና ከሀገር ውስጥ
1ኤች ዲ ፒ.ኢ. (HDPE PE100 Black)በኩንታል1
2ፒቪሲ ሬዚን (Polyethylene chloride)በኩንታል1
3ካልስየም ካርቦኔት (Calcium Carbonate)በኩንታል1
4ስታብላይዘር (Stabilizer)በኩንታል1
5ካርበን ብላክ (Carbone Black)በኩንታል1

ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው ግዴታዎች፡

  1. ህጋዊና በ2019 ዓ.ም. የታደሰ የጫኝና አውራጅነት ፍቃድ ያላችሁና የዘመኑን ግብር የከፈሉና የንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. ቫት፣ ቲን ወይንም ቲኦቲ ሠርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
  3. ህጋዊ የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል፣
  4. አንዱን ኩንታል የሚያወርዱበትንና የሚያደርድሩበትን ዋጋ ከላይ በተዘረዘረው መሠረት በኮምፒዩተር የተጻፈ ዋጋ ማቅረብ የሚችሉ፣
  5. ጥሬ ዕቃው በሚወርድበትና በሚደረደርበት ወቅት እንዳይፈስና እንዳይባክን ሙሉ ዋስትና መውሰድ የሚችሉ፣
  6. ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 2,000.00 (ሁለት ሺህ) በሲፒኦ (CPO) Oromia pipe Factory PLC በሚል ማስያዝ የሚችሉ፡

በመሆኑም ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚታሟሉ ተጫራቾች ከላይ የተዘረዘሩትን የፋብሪካ ጥሬ ዕቃ የምታወርዱበትና የምተደረድሩበትን ዋጋ በታሸገ ኤንቬሎፕ በማቅረብ መወዳደር ትችላላችሁ። ጨረታው ህዳር 25 ቀን 2019 ዓ.ም. ከቀኑ 8:00 ሰዓት ተዘግቶ ወዲያውኑ በ8:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ የሚከፈት ሲሆን ባይገኙም ያስገቡት የጨረታ ሰነድ ሌሎች ተጫራቾች በተገኙበት ተከፈቶ የሚታይ ይሆናል።

ማሳሰቢያ፡ ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፤ ቃሊቲ አሽከርካሪዎች ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ቅጥር ግቢ ጀርባ፤
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር-011-4-395-828 / 011-4-395-911

የኦሮሚያ ፓይፕ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግል ማህበር

Summary
Oromia Pipe Factory PLC (Kality, Addis Ababa) re-tenders loading, unloading and stacking of imported and local raw materials (HDPE, PVC resin, calcium carbonate, stabilizer, carbon black), priced per quintal. Licensed loading and unloading service providers may bid.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender