Tender Detail

Tender Details

  • Company Tsehay Insurance S.C (TISC) (ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ)
  • Address ቦሌ ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 25111111970
  • Websitehttps://tsehayinsurance.com/
  • Deadline29 Oct 2026, 10:00 AM
  • magazineሪፖርተር
  • Bid Document Price200(ሁለት መቶ ብር)
  • Bid Securityብር 10,000.00 (አስር ሺ ብር) በባንክ ክፍያ ማዘዣ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ደብዳቤ
  • opening dateበዕለቱ ጠዋት 4:15 ሰዓት
  • Categories Cleaning & Janitorial , Safety And Security , Labour Outsourcing Services

ፀሀይ ኢንሹራንስ አ.ማ ከታች የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች የሰው ኃይል አቅራቢ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለዋና መ/ቤት እና ለተለያዩ ቅርንጫፍ ቢሮዎቹ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

Tsehay Insurance S.C (TISC) (ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ)


ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ.

የሰው ሃይል አገልግሎት ግዥ ግልፅ ጨረታ

ቁጥር: ፀኢ/ግንአ/005/2019

ፀሀይ ኢንሹራንስ አ.ማ ከታች የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች የሰው ኃይል አቅራቢ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለዋና መ/ቤት እና ለተለያዩ ቅርንጫፍ ቢሮዎቹ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የቀረበውን የጨረታ መመሪያ እና መስፈርቶች የሚያሟሉ ማንኛውም ፍላጎት ያላቸው ተወዳዳሪዎች መወዳደር ይችላሉ፡፡

ሎት 1:- የጥበቃ አገልግሎት
ሎት 2:- የፅዳት አገልግሎት

  • ተወዳዳሪዎች ከሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሥራና አሰሪን ለማገናኘት የተሰጠ ሥራ ፈቃድ ያላቸውና ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  • የዘመኑን የመንግስት ግብር የከፈሉበትን የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ ተ.እ.ታ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት እና ታክስ ክሊረንስ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  • የጨረታ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ቦሌ ድልድይ የቀድሞ ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው 3ኛ ፎቅ የኩባንያው የፋይናንስ መምሪያ በመቅረብ፣ ከጥቅምት 09/2019 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 19/2019 ዓ.ም ድረስ የማይመለስ 200.00 ብር (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  • ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 (አስር ሺ ብር) በባንክ ክፍያ ማዘዣ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • የጨረታው ዋጋ የሚቆየው ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ90 ቀናት ይሆናል፡፡ ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡት ዋጋዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ያካተተ ሆኖ፣ ማንኛውንም ወጪና የመንግስት ቀረጥ የተከፈለባቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  • ግልጽ ጨረታው ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም ጠዋት 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ጠዋት 4:15 ሰዓት ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኩባንያው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡

ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ:- ፀሐይ ኢንሹራንስ አ.ማ ዋና መሥሪያ ቤት ቦሌ ድልድይ፣ የቀድሞው ብራስ ሆስፒታል ፊት ለፊት
ስልክ: +251 111 119 70 /71

✨ messages.ai_summary
Tsehay Insurance S.C. seeks licensed labor outsourcing providers for security (Lot 1) and cleaning (Lot 2) services at its head office and branch offices. Bidders must hold a Ministry of Labor and Social Affairs work license and submit renewed business license, VAT, TIN, and tax clearance certificates.
Save Tender