የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ሲሚንቶ ከለሚ ኢንዱስትሪ ወደ ደባርቅ ቢሂት መንገድ ስራ ፕሮጀክት ለማጓጓዝ የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ለመግዛት ያወጣው የጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር DCE/TR/170/2026)።
Defense Construction Enterprise (የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/SF/170/2026
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለደባርቅ ቢሂት መንገድ ስራ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል ሲሚንቶ ለማጓጓዝ የሚውል የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
| የዕቃው አይነት | መነሻ | መድረሻ | የጨረታ ቁጥር | የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት | የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት | የጨረታ ማስከበሪያ |
|---|---|---|---|---|---|---|
| ሲሚንቶ ማጓጓዝ | ለሚ ኢንዱስትሪ | ደባርቅ ቢሂት መንገድ ስራ ፕሮጀክት | DCE/ TR/170/2026 | ህዳር 23 ቀን 2019 ዓ.ም 4:15 ሰዓት | ህዳር 23 ቀን 2019 ዓ.ም 4:30 ሰዓት | 100,000.00 |
ስለሆነም ፡-
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የታደሰ የምስክር ወረቀት (ታክስ ክሊራንስ) እና የሀገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን ሚያረጋግጥ ኮፒ ወዘተ... ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ Bid Bond ማቅረብ ይኖርበታል። የጨረታ ማስከበሪያው እንደ ተጫራቹ ምርጫ በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠና የተረጋገጠ (C.P.O) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተዘረዘረው ዝርዝር መሰረት መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ቴክኒካል ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው ቀን እና ሰዓት በኢንተርፕራይዙ የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በሰንጠረዡ በተገለፀው መሰረት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ቃሊቲ ቶታል ማደያ ዝቅ ብሎ የቀድሞ መኮድ ግቢ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114-40-34-34
ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72
E-mail አድራሻ info@dce-et.com
የድረ ገፅ አድራሻ www.dce-et.com
ፖ.ሳ.ቁ 3414 ፋክስ ቁ.0114-40-04-71/0114-42-07-46
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
Summary
Defense Construction Enterprise seeks dry cargo transporters to haul cement from Lemi Industry to its Debark road construction project. Bidders need a renewed licence, VAT, TIN, tax clearance and supplier-list registration.
