Tender Detail

Tender Details


በስልጤ ዞን የሌራ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ የኤሌክትሪክ ዝርጋታ ዕቃዎች፣ የልብስ ስፌት ቁሳቁሶች፣ የስቴሽነሪ፣ የደንብ ልብስ፣ ኮምፒውተርና ላፕቶፕ፣ የደህንነት ካሜራ እና የጣውላ መሰንጠቂያ ማሽን ግዥ በ7 ሎት ያወጣው የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ።

የሌራ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ

Add to calendar Google Calendar Download .ics

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ሥራና ክህሎት ቢሮ ሥር በስልጤ ዞን የሚገኘው የሌራ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በ2019 በጀት ዓመት ለተቋሙ የስልጠና አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ቋሚና አላቂ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የዕቃዎች ዝርዝር (በሎት)፡-

  • ሎት 1፡- የኤሌክትሪክ ዝርጋታ ዕቃዎች
  • ሎት 2- ልብስ ስፌት ማሽን እና ለስፌት አገልግሎት የሚውሉ አላቂ ቁሳቁሶች
  • ሎት 3 የስቴሽነሪ (አላቂ የጽሕፈት መሳሪያዎች
  • ሎት 4፡-የጥበቃ የደንብ ልብስና ጫማ
  • ሎት 5፡-ኮምፒውተር እና ላፕቶፕ
  • ሎት 6፡-የደህንነት ካሜራ (Security Camera)
  • ሎት 7፡-የጣውላ መሰንጠቂያ ማሽን

ስለሆነም ተጫራቾች ለመጫረት ማሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-

  1. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በተዘጋጀው የአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ፣በመስኩ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ኮፒ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
  3. ተጫራቾች የተዘጋጀውን ሰነድ ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 (አስራ አምስት) የሥራ ቀናት ውስጥ በኮሌጁ ቢሮ ቁጥር 11 መውሰድ ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሰነድ የዋጋውን 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነዶች ኦርጅናልና ኮፒ በአንድ ላይ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 (አስራ አምስት) የሥራ ቀናት ውስጥ በቢሮ ቁጥር 11 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው ሳጥኑ በ15ኛው የሥራ ቀን ከቀኑ 10:30 ታሽጎ በቀጣዩ የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3:30 ላይ ይከፈታል /ማሳሰቢያ፡- 15ኛው ወይም በ16ኛው ቀን በዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሌራኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር 11 ይከፈታል።ተጫራቾች በራሳቸው ምክንያት ባይገኙ ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉለውም።
  7. አሸናፊ ተጫራቾች ውል ሲዋዋሉ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  8. መስሪያቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ
- በስልጤ ዞን ምዕራብ ፡ አዘርነት ፡ በርበሬ / ወረዳ የሌራ ፡ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ።
- መገኛው ከወልቂጤ ወደ ሆሳዕና በሚወስደው መንገድ ከወልቂጤ 150 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ወይም ከሆሳዕና ወደ ወልቂጤ በሚወስደው መንገድ 27 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል። ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች፡- 046 234 0341 / 0912 47 13 55 / 0925 64 65 20 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በስልጤ ዞን የሌራ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ

Summary
Lera Construction and Industrial College (Silte zone, Central Ethiopia) buys training items in 7 lots: electrical installation materials, sewing machines and supplies, stationery, guard uniforms and shoes, computers and laptops, security cameras and a timber sawing machine.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender