ፀዳል ኃ/የተ/ሁለገብ ኅብረት ሥራ ዩኒየን (ዱራሜ) የ2019/20 ምርት ዘመን የአፈር ማዳበሪያ ከማዕከላዊ መጋዘኖችና ከሞጆ ደረቅ ወደብ ወደ ከምባታ ዞን ወረዳዎች ለማጓጓዝ የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት ድርጅቶችን ለማወዳደር ለሁለተኛ ጊዜ ያወጣው ጨረታ ማስታወቂያ (ቁጥር ፀዩ/001/2019)።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፀዳል ኃ/የተ/ሁለገብ ኅብረት ሥራ ዩኒየን /ዱራሜ/
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ፀዩ/001/2019
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በከምባታ ዞን ዱራሜ ከተማ የሚገኘው ፀዳል ኃላፊነቱ የተወሰነ ሁለገብ ኅብረት ሥራ ዩኒየን የ2019/20 የምርት ዘመን በልግና መሐር እርሻ አገልግሎት የሚውል የአፈር ማዳበሪያ በዩሪያ ቁልቁ ከተማና ከሞጆ ደረቅ ወደብ ማዕከላዊ መጋዘኖች ወደ ከምባታ ዞን ወረዳዎች ከላስተር ጣቢያዎች ማጓጓዝ የሚችሉ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ትራንስፖርት ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ማጓጓዝ ይፈልጋል። ስለዚህ ተጫራቾች ከዚህ በታች ከ 1 እስከ 8 የተዘረዘሩ መስፈርቶች አሟልተው በመቅረብ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን በድጋሚ እናስታውቃለን።
- በዘርፉ ሕጋዊ፣ የታደሰ ፈቃድ ያለውና የዘመኑን ግብር ስለመከፈሉ መረጃና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማቅረብ የሚችል
- ከፈቃድ ሰጪ የመንግሥት መ/ቤት የሚመለስ ዋናና የማይመለስ ኮፒ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- በዘርፉ የሠራበትን የምስጋና ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚሆን 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ CPO ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል
- ጨረታውን የሚያሸንፍ ተጫራች የውል ማስከበሪያ ብር 250,000.00 ቅድሚያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በካሽ ማስያዝ የሚችል
- ተጫራቹ ለጭነት የሚያሰማራቸው ተሽከርካሪዎች ቢያንስ በአንድ ጊዜ 2000 ኩ/ል ማጓጓዝ የሚችሉትን ዝርዝር መረጃ ፈቃድ ከሰጣው የመንግሥት መ/ቤት በተሽከርካሪ አይነት፣ የሰሌዳ ቁጥር፣ የመጫን አቅም የያዘ መረጃ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል
- ለአስተዳደር ያመች ዘንድ ማንኛውም ተጫራች በአንድ ወረዳ ካሉት ጠቅላላ ከላስተር የማራገፊያ ጣቢያዎች ውስጥ በከፊል ዋጋ ሞልቶ ማቅረብ አይቻልም
- ተጫራች ከማዕከላዊ መጋዘኖች እስከ ማራገፊያ የወረዳ ጣቢያዎች ያለውን ጠቅላላ የጠጠርና አስፋልት መንገድ ድምር ርቀት ላይ የአንድ ኪሎ ሜትር የወረዳው ኪሎ ሜትር የወረዳው አማካይ ነጠላ ዋጋ በእያንዳንዱ ማራገፊያ ጣቢያ ደረጃ ሞልቶ ማቅረብ ይኖርበታል
ማሳሰቢያ
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ የማይመለስ 1500 ብር /አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር/ በመክፈል የድርጅቱ ክብ ማህተም ያረፈበትን የጨረታ ሰነድ (የሚጓጓዙ የምርቶች ዝርዝር፣ ከማዕከላዊ መጋዘን እስከ ማራገፊያ ቦታ ያለው የጠጠርና አስፋልት መንገድ ርቀት፣ ለመንገዱ የሚያስፈልግ የተሽከርካሪ ዓይነትና የወረዳ ነጠላ አማካይ ዋጋ መሙያ) የያዘ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከቢሮ ቁጥር 5 መግዛት ይችላሉ
- ተጫራቾች በሰም የታሸገ ኤንቨሎፕ/ፖስታ/ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት ወስጥ በክብ ማህተማቸው የተረጋገጠ የጨረታ ሰነድ በድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በድጋሚ ታትሞ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 7 የስራ ቀናት ክፍት ሆኖ በ7ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ 11:30 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ይታሸጋል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በድጋሚ ታትሞ በወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 7 ተከታታይ የስራ ቀናት(ቅዳሜና እሁድን ሳይካትት) በ8ኛው ቀን ከረፋዱ 4:00 ሰዓት በዩኒየኑ ጽ/ቤት በደፋ ይከፈታል። ሆኖም 8ኛው ቀን ቅዳሜ ና እሁድ ላይ ከዋለ ቀጥሎ ባለው ቀን የስራ ቀን (ሰኞ) ጨረታው ከላይ በተገለጸው ሰዓትና ቦታ ይከፈታል። በጨረታው በሚከፈትበት ቀን የሚገኙ ወኪል ተሳታፊዎች ከወከላቸው ድርጅት ህጋዊ ደብዳቤና ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነድ ጋር በአጫራቹ ድርጅት በማህተም የተረጋገጠው የተዘረዘሩ ግዴታዎችን ማሟላት ይጠበቅበታል
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
- አንዱ ተጫራች ሌላው ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይፈቀድም
አድራሻ፡- ከምባታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት
ስልክ፡- 0913478832/0912355938/0992001000/ 0916748108
ፀዳል ኃላፊነቱ የተወሰነ ሁለገብ ህብረት ሥራ ዩኒየን፡- ዱራሜ
Summary
Tsedal Multipurpose Cooperative Union (Durame) re-tenders the transport of fertilizer from central warehouses and Mojo dry port to Kembata zone woreda stations. Licensed dry cargo transporters able to move 2,000 quintals at once may bid.
