Tender Detail

Tender Details

  • Company Tsedey Bank S.C. (ፀደይ ባንክ አ.ማ)
  • Address ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት ህንጻ 16ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 09 ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115584896
  • Websitehttps://tsedeybank-sc.com/
  • Deadline26 Dec 2026, 9:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • CountryEthiopia
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid Securityየመነሻ ዋጋ 1/4ኛ በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲ.ፒ.ኦ በፀደይ ባንክ አ.ማ ስም
  • opening date17/04/2019 ዓ/ም ሐራጅ፤ ጎንደር አዘዞ ጠዳ ክ/ከተማ ፀደይ ባንክ ድማዛ ቅርንጫፍ
  • Sector Foreclosure , Business and Industry Foreclosure , House and Building , House and Building Maintenance

ፀደይ ባንክ አ.ማ ጎንደር ዲስትሪክት በአዋጅ ቁጥር 97/90 መሰረት በጎንደር ከተማ ቀበሌ 20 ኢንዱስትሪ መንደር የሚገኝ 1500 ካ.ሜ ስፋት ያለው የኢንዱስትሪ ሼድና ቦታ ታህሳስ 17 ቀን 2019 ዓ.ም በሐራጅ ለመሸጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ያወጣው ማስታወቂያ።

Tsedey Bank S.C. (ፀደይ ባንክ አ.ማ)

Add to calendar Google Calendar Download .ics

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ

ፀደይ ባንክ አ.ማ ጎንደር ዲስትሪክት ድማዛ ቅርንጫፍ ለወ/ሮ ሂሩት ታደለ ሉቃስ ለሰጠው ብድር በመያዣ የያዘውን ጎንደር ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 20 ኢንዱስትሪ መንደር ቁጥር 02 የካርታ ቁጥር 10580/2008 የቦታው ስፋት 1500 ካ.ሜ የሆነ የኢንዱስትሪ ሼድ እና ቦታ ለንፅህና እቃዎች ማምረቻ አገልግሎት የሚውል በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች ለጨረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደምቦች በመገንዘብ ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት ተጫራቾች እንዲጫረቱ ይጋብዛል።

  1. የቤቱ የጨረታ መነሻ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን ሳይጨምር ግምቱ 20,389,056.58 (ሃያ ሚሊዮን ሶስት መቶ ሰማንያ ዘጠኝ ሺህ ሃምሳ ስድስት ብር ከ58/100 የሆነ
  2. ተጫራቾች የቤቱን ጨረታ መነሻ ዋጋ ብር 1/4ኛ (በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲ.ፒ.ኦ) በጸደይ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  3. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠው የጨረታው ውጤት በሚመለከተው አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠው ብቻ ይሆናል።
  4. በጨረታው የሚሳተፈው በህግ ሰውነት ያገኘ ከሆነ የድርጅቱ መመስረቻ ጽሁፍ ወይም መተዳደሪያ ደምብ፤ ህጋዊ ሰውነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ህጋዊ ውክልና ማቅረብ አለበት።
  5. የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ10 ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈልና በጨረታ ያሸነፈውን ንብረት መረከብ ይኖርበታል። አሸናፊው በ10 ቀናት ውስጥ ገንዘቡን ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
  6. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ጥሬ ገንዘብ ወይም ሲፒኦ ይመለስላቸዋል።
  7. የጨረታ አሸናፊው ከሚገዛው ንብረት ዋጋ በተጨማሪ ከቤቱ ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፡ ግብር፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እና ከስም ዝውውሩ ጋር የሚገናኙ ማንኛውንም ወጪዎች ገዥ ይሸፍናል/ይከፍላል። ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሆኖ ለቀሪውና የክፍያ ጊዜው ላልደረሰ የሊዝ ክፍያ ገዥ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ጋር እንዲዋዋል ይደረጋል።
  8. ተጫራቾች ቤቱን/ድርጅቱን/ በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ።
  9. ጨረታው የሚካሄደው 17/04/2019 ዓ/ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6:00 ሰዓት ጎንደር ከተማ አዘዞ ጠዳ ክ/ከተማ ልዩ ቦታው ፀደይ ባንክ ድማዛ ቅርንጫፍ ሲሳይ ጋራዥ ፊት ለፊት ይሆናል።
  10. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ: ፀደይ ባንክ ድማዛ ቅርንጫፍ በስ.ቁ 0918077545 (0581140846) ይደውሉ።

ፀደይ ባንክ አ.ማ

Summary
Tsedey Bank S.C. Gondar District auctions foreclosed collateral under Proclamation 97/90: an industrial shed on a 1,500 sq m plot in the Kebele 20 industrial village, Gondar, used for producing hygiene products. Open to individuals and registered companies.
Not stated in the notice: bid document price. Check the original document or ask the issuer.
Save Tender Remind me on Telegram
Report a problem with this tender